የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

የአፍሪካ ሀገራት (የኢትዮጵያ  ፌዴራላዊ  ዴሞክራሲያዊ  ሪፐብሊክ)

በመጀመሪያ  አጭር ታሪካዊ  ዳሰሳ

– ኢትዮዽያ  ቀደምት እና ታሪክ ያላት  ለቀኝ ግዛት እጅ ካልሰጡ ሀገራቶች ውስጥ አንድዋ ስትሆን  ከ 1935 – 1941 ለስድስት ዓመታት ያህል  በጣሊያን  በሙሶሊኒ ዘመን  ቀኝ ግዛት ለመያዝ ሙከራ አድርጎዋል ። ነገር ግን የሰው ልጅና የጦር መሳሪያ ኪሳራ እንጅ ያተረፈው ነገር አልነበረም ። ኢትዮዽያ ቀደምት የታሪክ ስልጣኔ ያላት ሀገር ስትሆን ይህም ስልጣኔ ወደ ሁለተኛው ዘመን የአክሱም ስልጣኔ ይጠጋል ። 

– ኢትዮዽያ በተለያየ የታሪክ እርከን ውስጥ ያለፈች አገር ናት ። በዘመነ መንግስታቸው እጅግ ዝነኛ የነበሩት ዳግማዊ ሚኒሊክ በ1889 ዓ.ም  የሀገሪቱ ንጉስ ሆነው ተሾሙ ። በዚያን ጊዜም ከጣሊያን መንግስት ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራርመዋል ። አዲስ አበባም የኢትዮዽያ ዋና ከተማ ሆና የተቆረቆረችው በዘመነ መንግስታቸው ነበር ። ዳግማዊ ሚኒልክም በ1913 ዓ.ም በሞት ተለዪ ። 

– ንጉስ ነገስታት ሀይለስላሴም በ1928 ስልጣኑን ተረከቡ ። የስልጣን ዘውዳቸውን ከመረከባቸው በፊት ልጅ እያሱ በመባል ይጠሩ ነበር ። በ1930 ዓ.ም ላይ የንግስና ዘውዳቸውን ሲጭኑ ራስ ተፈሪ መኮንን የሚለውን ስያሜ አገኙ ። በሳቸው ዘመንም ነበር ጣሊያን ኢትዮዽያን ለመውረር ሙከራ ያደረገችው ።  

– በሃይለስላሴ ንግስና ዘመንም ከተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት መካከል በ1963 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤርትራ ፌዴራላዊ ሪፐብሊግ  ልዕልና የተጠበቀ መሆኑን ሲሆን ንጉስ ሀይለስላሴ ግን ኤርትራ አንዱ የኢትዮዽያ አካል መሆንዋን አወጀ ። 

– በዚህም ዘመን በ1963 ከተተገቡሩት ተግባራት መካከልም የመጀመሪያው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የስብሰባ ተካሄደ ሲሆን  የንጉስ ሃይለስላሴ ንግስናም እስከ 1974 ድረስ ቀጠለ ። በማስከተልም የሀገሪቱ ወታደር መፈንቅለ መንግስት በማድረግ " የመንግስቱ ሃይለመርያም " መንግስት ተከተለ ። 

የቀይ ሽብር ወቅት "1973/1974 –1991 


 – የመንግስቱ ሃይለማርያም የንግስና ጊዜም ከመጀመሩ በፊት 1975 ንጉስ ሃይለስላሴ ተገደሉ ። በ1987/1977 አዲሱ የመንግስቱ ሃይለማርያም የስልጣን ዘመን መጀመሪያ  ላይ ፈታኝ ነገራቶች ገጠሙት ከነዚህም መካከል በሀገሪቱ ውስጥ ብዙ ግጭቶች ተከሰቱ ። በሀገሪቱ ውስጥም ከፍተኛ ረሃብ ተከሰተ ። 

– መንግስቱም ሀይለማርያምም በ1987 በአዲሱ ሕገ–መንግስት ተመረጡ ።  በ1991 እ.ኤ.አ የመንግስቱም ሀይለማርያም የስልጣን ዘመን በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ግንባር አማካኝነት በሀይል ከስልጣን ወረደ ። መንግስቱም ሀይለማርያም ከሀገር ውጭ ሸሹ ። 

የአብዮታዊ ዲሞክራቲክ መንግስት የስልጣን ዘመን 

– እ.ኤ.አ ሐምሌ 1991 የሀገሪቱ የህዝብ ተወካዩች ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን በጊዚያዊነት ለሁለት ዓመት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾመ ። ከሁለት ዓመቱም ቡኃላ ከተለያዪ ፓርቲዎች ጋር ምርጫን ለማከናወን ተወሰነ ።  እ.ኤ.አ በ1995 በተደረገው የፓርላማ ምርጫ የቀድሞውን የኢትዮዽያ ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢህአዲግ)  ሊቀመንበር የሆኑትን አቶ/መለስ ዜናዊን ጠቅላይ ሚስትር አድርጎ ሲመርጥ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳን ፕሬዝዳንት አድርጎ መረጠ ።

– በዚህ ወቅትም ከተከናወኑ ዋና ዋና ክስተቶች መካከል ኤርትራ በ1994 እ.ኤ.አ ከኢትዮዽያ መገንጠልዋን ያወጀችበት ወቅት አንዱ ሲሆን  ሌላው ለእያንዳንዱ ክልሎች የራሳቸውን መብት በራሳቸው የመወሰን መብትን የሚያፀድቅ ህገ መንግስት የረቀቀበት ወቅት መሆኑ  ነው ። 
 – የኢትዮዽያ ወታደር ሱማሊያ 2006 ላይ የገባ ሲሆን በ2009 ላይም ሱማሊያን ለቆ ወቶዋል ። ባሁኑ ወቅትም የኢትዮዽያ ወታደር ከአፍሪካ ህብረት የፀጥታ አስከባሪ ወታደር  (አሚሶንም) ጋር በሱማሊያ ይገኛል ። 

– እ.ኤ.አ በጥቅምት 2001 ላይ አቶ ግርማ ወልደጎርጊስ የዶክተር ነጋሶ ጊዳዳን ቦታን ተክተው ተሾሙ ። ፕሬዝዳንት መለስ ዜናዊም ከዚህ አለም በሞት ሲለዪ እሳቸውን ተክተው አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመረጡ ። በግርማ ወልደጎርጊስ ቦታም ዶክተር ደመቀ መኮንን ተተኩ በ30/9/2012 ላይ አዲስ የተመረጡት አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ቃለ መሀላ ፈፀሙ ። በ2015 ግንቦት ወር ላይም የገዢው ፓርቲ  (አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባርም) ምርጫውን ማሸነፉን ይፋ አደረገ ።  ከዚሁ ጋር ተያይዞ ኢትዮዽያን በሁለተኛ እቅድ ለማልማት በሚል ዋና ከተማዋን አዲስ አበባን የማስፋት እቅድን ነድፎ መስራት ጀመረ ።  ይህንንም አዲስ አበባን የማስፋፋት የማስተር ፕላን ስራ ተቃውሞ ገጠመው በተለይም ከኦሮሚያ ብሔር ተወላጆች በዚህም አለመግባባት ከሀሪቱ ፖሊስ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት  140 ሰዎች እንደተገደሉም ይነገራል ። 

– በመቀጠልም በ2018 በገዢው ፓርቲ ውስጥ በተደረገ ምርጫ ዶክተር አብይ አህመድ በፕሬዝዳንትነት ተመረጡ  ። 

መልክዓምድር 

 • ኢትዮጵያ በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ ከ3-14 ዲግሪ ሰሜን እና ከ33-48 ዲግሪ ምሥራቅ የምትገኝ አገር ስትሆን የቆዳ ስፋቱዋም 1,127,127 ካሬ ኪ.ሜ. ነው።
 • በሰሜን ከኤርትራ፣ በምዕራብ ከሱዳን፣ በደቡብ ከኬኒያ፣ እንዲሁም በምሥራቅ ከጅቡቲ እና ከሶማሊያ ጋር ትዋሰናለች።
 • የኢትዮጵያ አብዛኛው ግዛት በተራሮችና በሀይቆች የተሞላ ሲሆን፣ ታላቁ የምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ እነዚህኑ ከፍተኛ ቦታዎች ከሰሜን ምሥራቅ ወደ ደቡብ ምዕራብ በመጋደም ለሁለት ይከፍላቸዋል። በስምጥ ሸለቆው ዙሪያም በረሃማ የሆኑ ዝቅተኛ ቦታዎች ይገኛሉ። ይኅን መሰሉ የመልክዓ-ምድር ልዩነት አገሪቷ የተለያዩ የአየር ንብረት፣ የአፈር፣ የዕፅዋት እና የሕዝብ አሰፋፈር ገጽታዎች እንዲኖራት አስችሏታል።   

 • በከፍታና በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ የተነሣ በኢትዮጵያ ውስጥ ሦስት ዐይነት የአየር-ንብረት ክልሎች ይገኛሉ። እነሱም:-
  • ደጋ - ከፍታቸው ከባሕር ጠለል 2400 ሜትር የሚጀምር እና የሙቀት መጠናቸው ከ 16 ዲግረ ሴ.ግ የማይበልጥ፤
  • ወይናደጋ - ከፍታቸው ከባሕር ጠለል ከ1500 እስከ 2400 ሜትር፣ ሙቀታቸውም ከ16 ዲግረ ሴ.ግ እስከ 30 ዲግረ ሴ.ግ የሚደርስና፣
  • ቆላ - ከባህር ጠለል በታች ጀምሮ እስከ 1500 ሜትር ከፍታ ያላቸው፣ የሙቀት መጠናቸውም ከ30 ዲግረ ሴ.ግ እስከ 50 ዲግረ ሴ.ግ የሚደርስ አከባቢዎች ናቸው።
 • ዋናው የዝናብ ወቅት ከሰኔ አጋማሽ እስከ መስከረም አጋማሽ ሲሆን፣ ከሱ ቀደም ብሎ አልፎ አልፎ የሚጥል የበልግ ዝናብ በየካቲት እና በመጋቢት ይከሰታል። የተቀሩት ወራት በአብዛኛው ደረቅ ናቸው   

ዋና ከተማ

 • የኢትዮጵያዋና ከተማ አዲስ አበባ ነው

  

አጠቃላይ ታሪክ   

 • ከጥንት ጀምሮ ከነበሩ አገሮች የምትመደብና በአፍሪካ ከሚገኙ አገሮች ከሁሉም የበለጠ ረጅም እድሜ ያስቆጠረች አገር ነች፡፡ አምስት ሚሊዮን አመት የሚሆነውና በጣም ረጅም እድሜ ያስቆጠረው የሰው ቅሪት የተገኘው በኢትዮጵያ አዋሽ ሸለቆ አካባቢ ሲሆን ይህም፣2 ሚሊዮን አመት የሆነውን እዛው አካባቢ የተገኘውን የሉሲን /ድንቅነሽን/ አጽም በእድሜ ይበልጣል፡፡
 • በአራተኛው ክፍለ ዘመን ከግብጽና ሶሪያ ሚሲዮኖች መጥተው ክርስትናን ለኢትዮጵያ አስተዋውቀው ነበር፡፡ ነገር ግን በሰባተኛው ክፍለ ዘመን በእስልምና መስፋፋት ምክንያት ኢትዮጵያ ከአውሮፖውያኑ ክርስትና ርቃ ቆይታለች፡፡ ከዛም በ1500 ዎቹ ፖርቱጋሎች በህንድ ውቅያኖስ ላይ የነበራቸውን ይዞታ ለማጠናከርና ኢትዮጵያ ውስጥ የሮማ ካቶሊክን ለማስፋፋት ሲሉ ከኢትዮጵያ ጋር የነበራቸውን ግንኙነት መልሰው ጀምረው ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት አንድ ክ/ዘመን ያህል የፈጀ የሀይማኖት ግጭት በ1630ዎቹ ተነስቶ ከውጪ የመጡትን ሚሲዮናዊያንን በሙሉ ከኢትዮጵያ ተባረው ሲወጡ ተፈጽሟል፡፡ ይህ የከፋ የግጭት ጊዜ ኢትዮጵያ የውጭ ክርስትያኖች ላይ እና አውሮፖውያኖች ላይ እስከ ሀያኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ፊቷን እንድታዞር አስተዋጾ ከማድረጉም በተጨማሪ እስከ 19ኛው ክ/ዘመን አጋማሽ ድረስ ኢትዮጵያ ከመላው አለም ተገልላ እንድትቆይ አድርጓታል፡፡
 • ከ1700ዎቹ ጀምሮ 100 ለሚሆኑ አመታት ኢትዮጵያ ማዕከላዊ አገዛዝ ሳይኖሯት ቆይታለች፡፡ ይህም "የመሳፍንት ዘመነ መንግስት" የተለያዩ የኢትዮጵያን ክፍል ይገዙ በነበሩ ገዢዎች መሀል በነበረው ፉክክር የተነሳ በመጣው ብጥብጥ ሲታወቅ በ1869 ግን አፄ ቴዎድሮስ መሳፍንቶችን አንድ ላይ በማምጣት ዋነኛ አሰባሳቢ ሀይል ሆነዋል፡፡ ተከታያቸው አፄ ዮሀንስም አፄ ቴዎድሮስ የጀመሩትን ቀጥለው ኢትዮጵያን ለመውረር ሙከራ ያደረጉትን ደርቡሾችና ሱዳኖችን ረተው መልሰዋል፡፡ 

 

 • ከ1881 እስከ 1905 ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ በአፍሪካ ይዞታቸውን እያሰፉ የነበሩትን የአውሮፖ ሀይሎችን ጥቃት በመከላከል ኢትዮጵያን ገዝተዋል፡፡ በዛ ጊዜ ጣልያን ኤርትራን በከፊል ቅኝ ገዝታ የነበረችበትና በ1880ዎቹ አጋማሽ ላይ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ቅኝ ገዝታት የነበረችበት ጊዜ ስለነበር ከሌሎች አውሮፖ አገራት በበለጠ ለኢትዮጵያ አስጊ ነበረች፡፡ በ1880 ግን እስከዛሬ ድረስ ዝነኛ በሆነው የአድዋ ጦርነት ኢትዮጵያ ጣልያንን አሸንፋ በአፍሪካ የቀኝ ገዥ ሀይሎችን ያሸነፈች የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች፡፡

 • በ1908 የክርስትና ሀይማኖት ሹማምንት ልጅ እያሱን ለእስላሙ ህብረተሰብ በመቆርቆራቸው ምክንያት ከስልጣን አውርደው የዳግማዊ ሚኒሊክ ልጅ የሆኑትን እቴጌ ዘውዲቱን ስልጣን ላይ አውጥተዋቸዋል፡፡ የሳቸው የቅርብ የስጋ ዘመድ የነበረውም ራስ ተፈሪ መኮንንም ሞግዚት አስተዳደርና ወራሽ ሆነው ተሹመዋል፡፡

 • እቴጌ ዘውዲቱ በ1922 ሲሞቱ ተተኪያቸው ስማቸውን ወደ ሀይለስላሴ በመቀየር ስልጣን ላይ ወጡ፡፡ ነገር ግን በ1928 ዓ.ም የጣልያን ሀይሎች ኢትዮጵያን ለአጭር ጊዜ ወረው ሲቆጣጠሩ ግዛታቸው ተቋርጦ ነበር፡፡ ይህን ጊዜም አፄ ሀይለስላሴ ለሊግ ኦፍ ኔሽንስ ይግባኝ ብለው ሰሚ ስላጡ ወደ እንግሊዝ ተሰደው ለሚቀጥሉት አምስት አመታት የኢትዮጵያ አርበኞች ከብሪታንያ ጋር በመተባበር ጣልያንን እስኪያሸንፉ ድረስ ወደ ስልጣናቸው አልተመለሱም ነበር፡፡

 • አፄ ሀይለ ስላሴ እስከ 1966 ድረስ ስልጣን ላይ ከቆዩ በኋላ በምትካቸው የጊዜአዊ ወታደራዊ ምክር ቤት /ደርግ - ኮሚቴ የሚል ትርጉም ሲኖረው/ ስልጣን ይዘው በስም ሶሻሊስት የሆነ በአቋም ግን ወታደራዊ አመራር ያለው መንግስት ተመሰረተ።ከዚህ ክስተት በኋላ ሻለቃ መንግስቱ ሀይለ ማሪያም እንደ ኘሬዝዳንትና እንደ ደርግ ሊቀ መንበር ስልጣን ያዙ፡፡

    በ1980ዎቹ መጀመሪያ በኢትዮጵያ በተለይ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በሚገኙት ትግራይና ኤርትራ መንግስታዊ ግልበጣ ተካሄደ፡፡ በ1981ዓ.ም የትግራይ ህዝቦች ነፃ አውጪ ግንባር /ትህነግ/ ከብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ብአዴን/ እና ከኦሮሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ኦህዴድ/ ጋር አንድ ላይ በመሆን የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር /ኢህአዴግ/ን መሰረቱ በግንቦት 1983 ላይም የኢህአዲግ ሀይሎች ወደ አዲስ አበባ በመግባት ኮሎኔል መንግስቱ ወደ ዙንባቢዌ እንዲሰደድ ሆኗል፡፡

 • በ1983 ከኢህአዲግ እና ሌሎች የአገሪቷ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተውጣጡ 87 የተወካዮች ምክር ቤትና በሽግግር ህገ መንግስት የኢትዮጵያ ሽግግር መንግስት ተቋቋመ፡፡
 • በዛው አመት በኢሳያስ አፈወርቂ መሪነት የኤርትራ ህዝቦች ነፃ አውጭ ግንባር /ኤህነግ/ ከ30 አመታት ትግል በኋላ ኤርትራን ተቆጣጥሮ ጊዜአዊ መንግስት መሰረተ፡፡ እስከ ግንቦት 1985 ዓ.ም ድረስም ኤርትራዊያኖች በተባበሩት መንግስታት ክትትል የጠየቁት የመገንጠል መብታቸውን እስኪያገኙ ድረስ የጊዜአዊው መንግስትም ስልጣን ላይ ቆየ፡፡

በኢትዮጵያም ኘሬዘዳንት መለስ ዜናዊና የሽግግር መንግስቱ አባላት በሰኔ በ1986 ዓ.ም 548 አባላት ባሉት ለህገ መንግስታዊ ምክር ቤቶች ምርጫ ተካሄደ፡፡ በ1987ዓ.ም መጀመሪያ ላይ የተመረጡት የምክር ቤቱ አባላት የኢፌዲሪን ህገ መንግስት ተቀበሉ፡፡ የፖርላማ ምርጫ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው በ1987 ዓ.ም ሲሆን በዛው አመት ነሀሴ ወር ላይ መንግስት ተቋቋመ ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊም ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመረጡ።

 • ጠቅላይሚንስቴር መለስ ዜናዊ ነሃሴ 14፣ 2004 ዓም ከዚህ አለም በሞት ሲለዩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር የነበሩት ኃይለማርያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆነው ተሾሙ።

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በፓርቲው ውሰጥ በተደረገ ምርጫ ታህሳስ 2018 ላይ ጠቅላይ ሚኒስቴር የነበሩትን ኃይለማርያም ደሳለኝ ተክተው ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆነው ተሾሙ።

የመንግስት አወቃቀር  

 • ኢትዮጵያ የፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት አወቃቀር ሲኖራት በ9 የብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት እንዲሁም በሁለት የከተማ መስተዳድሮች የተዋቀረች ነች፡፡ አወቃቀራቸውም በሕገ መንግስቱ በተደነገገው መሰረት «በህዝብ አሰፋፈር፣  ቋንቋ ፣ ማንነት እና ፈቃድ ላይ» ተመስርቶ ሲሆን ክልሎቹም የሚከተሉት ናቸው።
  1. የትግራይ ክልል
  2. የአፋር ክልል
  3. የአማራ ክልል
  4. የኦሮሚያ ክልል
  5. የሶማሌ ክልል
  6. የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል
  7. የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል
  8. የጋምቤላ ክልል
  9. የሀረሪ  ክልል 
  10. በተጨማሪም የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ መስተዳደሮች ይገኙበታል።

 

 • እነዚህ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት አንዲሁም ሁለቱ የከተማ መስተዳደሮች በ800 ወረዳዎቸና ወደ 15000 በሚጠጉ ቀበሌዎች(5000 የከተማና 10000 የገጠር) የተከፋፈሉ ናቸው።

ህዝብ 

 • በ1999  ዓ.ም በተደረገውየህዝብና ቤት ቆጠራ እና ትንበያ መሰረትም 90 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ የነበር ሲሆን በ 2017 በተደረገ ጥናት 105.7ሚሊዮን እንደሆነ የህዝብ ቆጠራው ያመላክተል ይህ ማለት በአፍሪካ ውስጥ ከናይጀሪያ ቀጥሎ ሁለ፡፡ ከዚህም ውስጥ ወደ 84 ከመቶ የሚጠጋው በገጠሪቱ የኢትዮጵያ ክፍል ሲኖር የተቀረው በከተማና ከፊል ከተማ በሆኑ ቦታዎች ይኖራል፡፡ 
 • ኢትዮጵያ ከ80 በላይ የሚሆኑ ብሄር ብሄረሰቦች የሚገኙባት ሀገር ነች። የኦሮሞ፣ የአማራ፣ እና የትግራይ እንዲሁም የሶማሌ ብሄረሰቦች ከጠቅላላው የአገሪቱዋ ሕዝብ ቁጥር ክ3/4ኛ በላይ የሚሆነውን ይይዛሉ።
 • በሃይማኖት በኩልም ክርስትናና እስልምና በስፋት የሚስተዋልባት አገር ናት። እስልምና ከ 25-30% ፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተከታዮች ከ 60-65% ፡ ፐሮቴስታንት ደግሞ 10% የሚሆነውን ድርሻ ይሸፍናል።
 • የወንድአማካኝ እድሜ42 ዓመት ሲሆን የሴት ደግሞ 55.42 ዓመት ነው።
 • የዕድሜ ስብጥር (በመቶኛ)
  • 0-14 አመት - 42.8%
  • 15-19 አመት- 10.5%
  • 20-49 አመት- 37.4%
  • 50-59 አመት- 4.9%
  • 60 and above: 4.4%

 

ቋንቋዎች 

 • በኢትዮጵያ ውስጥ ከ80 በላይ ብሄር ብሄረሰቦች የሚኖሩ ሲሆን በቋንቋም በኩል ከ80 በላይ የሚሆኑ ቋንቋዎች የሚነገርባት ሀገር ናት፡፡
 • በአሁኑ ወቅት በእብዛኛው ኢትዮጵያውያን የሚነገሩት ቋንቋዎች አማርኛ እና ኦሮምኛ ሲሆኑ፤ አማርኛ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ነዋሪዎች የመማሪያ፤ የመገበያያ እንዲሁም የስራ ቋንቋ ሆኖ የቆየ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት የብሄራዊ ቋንቋ ነው።
 • በኢትዮጵያ የሚነገሩት ቋንቋዎች ወደ አራት ዋና ዋና የቋንቋ ክፍሎች ሊካተቱ ይችላሉ። እነዚሁም:-
  • ኩሻዊ: ወደ 19 ቋንቋዎችን የያዘ
  • የአባይ-ሰሃራዊ: ወደ 20 ቋንቋዎችን የያዘ
  • ኦሞአዊ: ወደ 23 ቋንቋዎችን የያዘና
  • ሴማዊ: ወደ 12 ቋንቋዎችን የያዙ ናቸው።
 • ኩሻዊ ከሚባሉት ቋንቋዎች ዋና ዋናዎቹ ኦሮምኛ፣ ሶማልኛ፣ አፋርኛ፣ ሲዳምኛ፣ ሃዲያኛ እና ከምባትኛ ሲሆኑ ከአባይ-ሰሃራዊ የቋንቋ ምድብ የሚካተቱት በርታኛ፣ ኩናማኛ፣ ጉሙዝኛ፣ ሙርሲኛ እና የመሳሰሉት ናቸው። እንደ ወላይትኛ፣ ጋሞኛ፣ ከፋኛ፣ ሃመርኛ የመሳሰሉት የኦሞአዊ ቋንቋ ዘሮች ሲሆኑ አማርኛ፣ ትግርኛ፣ ጉራጊኛ፣ ስልጢኛ፣ ሀደሪኛ እና መሰል ቋንቋዎች ከሴማዊ ቋንቋዎች ይመደባሉ።
 • የሴሚቲክ ምንጭ ያላቸው እንደ አማርኛ ያሉት ቋንቋዎች የራሱ የሆነ የተለየ የፊደል ስርአት ያላቸው ሲሆን ይህም ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ብቸኛዋ ባለ ጥንት ፊደል ሀገር ያደርጋታል። እነኚህ የሴሚቲክ ምንጭ ያላችው ቋንቋዎች ግዕዝ የተባለ በአሁኑ ወቅት ከቤተክርስትያን ውጭ ለእለት ተእለት ግልጋሎት ላይ የማይውል ግንድ ዘር አላቸው።

 

ኢኮኖሚ   

 • የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በዋነኛነት በግብርና ዘርፍ የተያዘ ነው ከዚህም ከሀገሪቱ ጠቅላላ የውስጥ ምርት 45 ከመቶውን ይሸፍናል፣ 10 ከመቶ የሚሆነው የኢንዱስትሪ ዘርፍ ሲሆን፣3 ከመቶው ደግሞ የማምረቻው ዘርፍ ይይዛል፡፡
 • የወጪ ንግድምየሚከናወን ሲሆን ከዚህም ውስጥ እስከ 60 ከመቶ የሚደርሰው የቡና መላክ ወጪ ንግድ ነው፡፡

ግብርና

 • እርሻ የአገሪቱ የጀርባ አጥንት ሲሆን አገሪቱ ከዚሁ የኢኮኖሚ ዘርፍ ቡና፣ የቅባት እህሎች፣ አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ስኳር እና የከብት መኖ ወደ ውጭ ትልካለች፡፡
 • ከዚህም በተጨማሪ የከብት ሀብት ልማት በመኖሩ ከዚህ ዘርፍ የቁም ከብት፣ ቆዳና ሌጦ በመላክ የውጭ ምንዛሬ ታገኛለች፡፡
 • ኢትዮጵያ ካሏት አጠቃላይ ዘርፎች ውስጥ የግብርና ዘርፍ ቀዳሚውን ሲይዝ በ2006/07 ዓ.ም በተገኘ አመታዊ ስሌት መሰረት ግብርና9 ከመቶ የሚሆነውን የሀገሪቱ የምርት ውጤት ይሸፍናል፡፡ ወደ 45 ከመቶ የሚሆነው የሀገሪቱ መሬት ለግብርና ስራ ምቹ ነው፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ወደ 10‚556 ሄክታር መሬት ብቻ ለእርሻ አገልግሎት የዋለ ነው፡፡

 

 • የአምራች ዘርፍ
  • በ2006/07 ዓ.ም3 ከመቶ የሚሆነውን የሀገሪቱን ጠቅላላ ምርት ያስመዘገበው ይህ ዘርፍ ነው፡፡ ከዚህም ዘርፍ የምግብ፣ የለስላሳ መጠጦች፣ የጨርቃ ጨርቅና የቆዳና ሌጦ ውጤቶች ይገኙበታል፡፡
  • ዘርፉ በዋነኛነት ከግብርና የሚገኙ ምርቶችን ለማቀነባበር እና ለማምረት ይንቀሳቀሳል፡፡ በዚህም ለሀገር ውስጥ ገበያ የሚውሉ የሸማቾች እቃዎችን ያቀርባል፡፡ ወደ ውጭ ከሚላኩ ምርቶችም ጨርቃ ጨርቅ፣ የታሸገና የቀዘቀዘ ስጋ፣ በከፊል የተጨረሱ ቆዳና ሌጦ፣ ስኳርና ሞላሰስ፣ የእግር አልባሳት፣ ትንባሆ፣ ለስላሳ መጠጦች፣ ዘይት፣ ሰም ፣ ሌዘርና የሌዘር ውጤቶችን ያቀርባል፡፡
 • አገልግሎት ሰጪ ዘርፍ
  • የአገልግሎት ሰጪ ዘርፍ5 ከመቶ የሚሆነውን የሀገር ውስጥ ምርት ይሸፍናል፡፡ ይህ ዘርፍ በአሁኑ ወቅት ቀስ በቀስ በማደግ ላይ የሚገኝ ሲሆን በ1996/97 ዓ.ም ከነበረበት 36 ከመቶ በ2006/07 40.8 ከመቶ ሊደርስ ችሏል፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው በተፈጠረው የትምህርት፣ የሪል-እስቴት፣ የኪራይ እና የንግድ እንቅስቃሴዎች፣ በጅምላና ችርቻሮ ንግድ፣ እንዲሁም የሆቴልና ሬስቶራንት ንኡስ-ዘርፎች እድገት ምክንያት ነው፡፡

የመገበያያ ገንዘብ

 • የኢትዮጵያየገንዘብ መለኪያ ብር ነው
 • 1 ብር ከ100 ሳንቲሞችጋር እኩል ነው
 • የብር ኖቶች

 

 

 

 

 • የመዳብ ሳንቲሞች፡ 1፣5፣10፣25፣ እና 50 ሳንቲሞች
 • የውጭ ምንዛሬ አገልግሎት በአየር መንገዶች እና ፈቃድ ባለቸው ሆቴሎች ይገኛል፡፡