የኮንጎ ድሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
 የኮንጎ ድሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

ኮንጎ ድሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

   ኮንጎ ድሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በመካከለኛው አፍሪካ የምትገኝ አገር ስትሆን አንዳንዴ -ኮንጎ ኪንሻሳ- በመባል ትታወቃለች፡፡ ይህውም በዋና ከተማዋ ስም የምትሰየምበት ሲሆን አንዳንዴ -ኮንጎ ብራዛቪል- በመባል ከምትታወቀው ኮንጎ ሪፐብሊክ ለመለየት ነው፡፡ በቆዳ ስፋቷ በአፍሪካ ደረጃ ሁለተኛ ስትሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ዐሥራ አንደኛውን ድረጃ ይዛ ትገኛለች፡፡

 

ይህችን በመካካለኛው አፍሪካ የምተገኘውን ኮንጎ ድሞክራሲያዊ ሪፐብሊክን በስተሰሜን ማእከላዊ አፍሪካና ደቡብ ሱዳን፣ በስተምስራቅ ኡጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ቡሩንዲና ታንዛኒያ፣ በስተደቡብ ዛምቢያና አንጎላ እንዲሁም በስተምዕራብ ኮንጎ ሪፐብሊክና በደቡብ ምዕራብ አንትላንቲክ ውቅያኖስ ያዋስኗታል፡፡

የአየር ጠባይ

የኮንጎ ድሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አየር ሁኔታ ሲታይ ኤክዋቶራላዊ አየር ጠባ ሲሆን ዓመቱን ሙሉ እጅግ ሞቃታማና በወበቅ የተሞላ ነው፡፡

ተራራዎቿ 

ኮንጎ ድሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በዓለም አቀፍ ደረጃ ብዙም ያልታወቀች አገር ስትሆን በዚሁ ደረጃ ያልታወቁ ደኖችም አሏት፡፡ አብዛኛው የኮንጎ ምድር በጥቅትቅ ደን የተሸፈነ ነው፡፡ ከዚህ ከጥቅትቅ ጫካ ወደለምለሙ የኒያሪ ወንዝ የሚያደርስ ሰፊ ሳህል -ሜዳማ ቦታ- ይገኛል፡፡ ይህው በአትላንቲክ ውቅያኖስ መጠነኛ ርዘመት ያለው ሳህል ነው፡፡ የኒያሪ ወንዝ ደግሞ ይህን የባህር ዳርቻ ሳህል ከማእከላዊው የሀገሪቱ ተራራማ ክፍል ይለየዋል፡፡ በርካታዎቹ የሀገሪቱ ደኖች የተላያዩ የዛኢር ወንዝ ገባሮች በሐገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል ወደደቡብ በኩል  እስከ ሰታንሊ ሀይቅ ደረስ ይፈሱባቸዋል፡፡

የኮነረጎ ድሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ወናዋና ከተሞች፤

ብራዛቪል

ኒካይ ከተማ

ሎዮሞ ከተማ

ዋናዋና ወደቦች፤

ቡዋንት ወደብ

ኑዋር ወደብ

የኮንጎ ድሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መዲና፤

Kinshasa (ኪንሻሳ)

 

የሀገሪቱ የመገባያ ገንዘብ

የኮንጎ ፍራንክ  (CDF)   

የሀገሪቱ ቋንቋዎች

የሀገሪቱ ብሄራዊ ቋንቋ ፈረንሳይኛ ነው፡፡ ሊንጋላ የሀገሪቱ የንግድ ቋንቋ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ኪንጉዋና ቋንቋ የሰዋሂሊ ቋንቋ ቀበልኛ ነው፡፡ እንዲሁም ኬኮንጎና ቺሎባ የተሰኙ ቋንቋዎችም አሉ፡፡

 

የሀገሪቱ አስተዳደር

የኮንጎ ድሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስተዳደር ሪፐብሊካዊ ነው፡፡

 

የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላ

የኮንጎ ድሞክራሲያዊ መንግስት እ.ኤ.አ. በ2006 ከተለምዶው የአፍሪካ ቀለማት ቀይ -ማህሉ ወርቃማ ኮከብ ያለበት- ና ብጫ የተዋቀረውን አዲሱን ሰንደቅ ዓላማ የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ አድርጎ ስይሟል፡፡

 

የኮንጎ ድሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መሪ

ፕሬዝዳንት ጆዜፍ ካቤላ ናቸው፡፡  

የህዝብ ቁጥር፡

እ.ኤ.አ. በ2017 በተካሄደው የህዝብ ቆጠራ የኮንጎ ድሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ነዋሪዎች ቁጥር 81.34 እንደደረሰ ተመልከቷል፡፡

የሀገሪቱ ብሄራዊ ባእል፡

በኮንጎ ድሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በየዓመቱ እ.ኤአ. ጁን 30 የሀገሪቱ የነፃነት ቀን ይከበራል፡፡

የኮንጎ ድሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ታሪክ

   ኮንጎ ድሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በፈረንሳይ ይተዳደር የነበረው የኤክዋቶሪያል አፍሪካ ክልል አካል ነበረች፡፡ በዚያን ወቀት ማእከላዊ ኮንጎ በመባል ትታወቅ ነበር፡፡ኮንጎ ነፃነቷን ያገኘችው እ.ኤ.አ. በ1960 ነበር፡፡ የኮንጎ ድመክራሲያዊ ሪፐብሊክ መሪ በህዝብ የሚመረጥ ፕሬዝዳንት ሲሆን የሀገሪቱ ከፍተኛ ስልጣን በሱ እጅ ይሆናል፡፡ የስልጣን ዘመኑም አምስተ ዓመት ይደርሳል፡፡ በህዝብ የተመረጠው የኮንጎ መሪ ተግባራቱን ለማከናወን የሚግዙትን የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስተርና የሚኒስተሮችን ቡድን ሰይመው ይሾማሉ፡፡ የኮንጎ ፓርላማ ሁለት ዋናዋና ክፍሎች ያሉት ሲሆን አንደኛው የህግ መምሪያ ምክር ቤት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ብሄራዊ ምክር ቤት ነው፡፡የብሄራዊ ምክር ቤት መቀመጫ ወንበር 125 የሚደርስ ሲሆን ሁሉም አባላት በህዝብ የተመረጡ መሆን አለባቸው፡፡ የስልጣን ዘመናቸውም አምስት ዓመት ይደርሳል፡፡የህግ መምሪያ ምክር ቤት ደግሞ በክልላዊ ምክር ቤቶች አማካይነት የሚመረጥ ሲሆን የአባላቱ ቁጥር 60 ይደርሳል፡፡ የስልጣን ዘመናቸው ደግሞ ስድስት ዓመታት ይደርሳል፡፡

የኮንጎ ድሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኢኮኖሚ

በተፈጥሮ ሀብት እጅግ የታደለች የሆነችው የኮንጎ ድሞክራሲያዊ  ሪፐብሊክ ኢኮኖሚ የማዝገም ሥራውን እንደቀጠለ ነው፡፡ እ.ኤ.አ. በ1960 ሀገሪቱ ነፃነቷ ከተጎናጸፈች ጀምሮ የተስፋፋው የተቀናጀ ሙስና፣ የሰፈነው አለመረጋጋት፣ እንዲሁም በዘጠናዎቹ መጀመሪያ የተቀሰቀሰውና እስካሁንም በተቆራረጠ መልኩ የቀጠለው ግጭት የሀገሪቱን ብሄራዊ ገቢና የመንግስት የገቢ ምንጭ በአስጊ ደረጃ እንዲቀንስ፣ እንዲሁም የሀገሪቱ የውጭ እዳ በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር አድርጎታል፡፡ በሀገሪቱ የሰላም ስምነት ከተፈረመ በኋላ በ2003 የሸግግር መንግስት እንደተዋቀረ መንግስት ከአለም አቀፍ የፋይናነስ ተቋማትና ከአለም አቀፍ ለጋሽ ወገኖች ጋር የነበረውን ግንኙነት እንደገና እንዲቀጥል በማድረጉ የኮንጎ ኢኮኖሚ ያዘገመም እንኳ ቢሁን መሻሻል ጀምሯል፡፡ ፕሬዝዳንት ከቤላ የጀመሩት የተሃዲሶ አንቅስቃሴ በሀገሪቱ በአላው የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ በተንሰራፋው ሙስናና ወገናዊነት ምክኒያት የሚያስመዘግበው ውጤት እጅግ ውስን መሆኑ ተመልክቷል፡፡ ይህም ሁኔታ ወደሀገሪቱ የሚገባውን አለም አቀፍ የኢምቨስትመንት ፍሰት አድማስ አጅግ ጠባብ እንዲሆን አድርገጎታል፡፡

   የሀገሪቱ የገቢ መንጭ ዋልታ የሆነው የማዕድን ዘርፍ እንቅስቀሴ በአዲስ መልኩ በመጀመሩ ምክኒያት አስከ 20015 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ የኪንሻሳ የፋናንስ አቋም እንዲጠናከር እንዲሁም የሀገር ውስጥ ገቢው አንዲጨምር አደርጓል፡፡ ነገር ግን በዚያን ወቅት የተከሰተው የሸቀጥ ዋጋ መቀነስ ልማቱ እንዲጓተት፣ የገበያ ግዝበት እንዲፈጠር፣ የሀገሪቱ ግንዝብ ዋጋ አንዲቀንስና የፋይናንስ እጥረት እንዲከሰት አድርጓል፡፡ በኮንጎ ያለው ያልተጠናከረ የህግ ማእቀፍ፣ የተስፋፋው ሙስናና በመንግስት ፖሊሲ የሚታው የግልጽነት መጓደል ለሀገሪቱ የማዕድን ዘርፍና አጠቃላይ ኢኮኖሚ የማያቋርጥ ውዝግብ እየፈጠሩ ይገኛሉ፡፡ ሆኖም በአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ገቢ መርጃ ቦታ የሌላቸው በርካታ ተላላቅ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች በሀገሪቱ እንደሚካሄዱ ይታመናል፡፡

   በኮንጎ ድሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ድህነት በከፍተኛ ደረጃ ተስፋፈቱ አንደቀጠለ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እሰከ 2015 ተነድፎ የነበረው የሚሊኒየም የልማት እቅዶችም እንደከሸፉ ተረጋግጧል፡፡ ኮንጎ ድሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በ20015 ከአለም የገንዘብ ድርጂት ጋር የነበረውን ውልም በዚሁ መልኩ አጠናቃለች፡፡ የነሀስ ዋጋ መቀነስ በተለይም በ2016ና 20017 የተከሰተው ዋጋ ቅናሽ በኮንጎ ኢኮኖሚ ከፍተኛ ተጽእኖ አሳድሯል፡፡ በመሆኑም የመንግስት ገቢና ወጭ የተጠባባቂ የውጭ ምንዛሬ መጠን በከፍተኛ ደረጃ አሽቆልቁሏል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በ2017 አጋማሽ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ግዥበት 50% አካባቢ ደርሶ ነበር፡፡ የሀገሪቱ ግዥበት ከ2000 ጀምሮ በዚህ መልኩ ሲወጣ የመጀመሪያ ጊዜው ነበር፡፡

    የኮንጎ ድሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ነዋሪዎች ኢኮኖሚ በዋናነት ማዕድናትን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ በሀገሪቱ ካሉ ማዕድናት መዳብ የመጀመሪያውን ደረጃ ይይዛል፡፡ ኮንጎ ከመዳብ አምራች አገሮች ግንባር ቀደም ሆና የምትጠቀስ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ከሰው ሰራሻ አልማዝ አምራች አገሮችም ትመደባለች፡፡ ኮነጎ ከአለም የማዕድን አምራች አገሮች ሁለተኛውን ደረጃ ይዛ ትገኛለች፡፡ ኮንጎ በሀገሪቱ ባህር ዳርቻ አካባቢ የባህር ውስጥ ነዳጅም ታመርታለች፡፡ በሀገሪቱ ከሚመረቱ ከፍተኛ እሴት ካሏቸው ማዕናት ካድሚዮም፣ ኮፓልት፣ ወርቅ ማንጀኒዝ፣ ብር፣ ቀስድርና ዚንክ ናቸው፡፡

 

እርሻና ደኖቿ

   የኮንጎ እርሻ ዘርፍ እንቅስቃሴ በዝቅተኛ የእርሻ መጠኖች የተመሰረተ ነው፡፡ በመሆኑም የሀገሪቱ ገበሬ ቤተሰቦች የእለት ተእለት ኖሯቸውን ለማሸነፍ ከፍተኛ ትግል ያደርጋሉ፡፡ በሀገሪቱ ከሚመረቱ ዋናዋና የእርሻ ምርቶች ሙዝ፣ ካሳፋ፣ ብጫ በቀሎ፣ ኦቾሎኒና ሩዝ በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳሉ፡፡ በገበያ ምርቶች ደገሞ ካካው. ቡናና ሻይ ቅጠል ይካተታሉ፡፡ ከዝናባማው ከኤክዋቶራል ደን ምርቶች ውስጥም የዘምባባ ዘይት፣ ላስቲክና እንጨት ምርቶች ይካተታሉ፡፡

ኢዱስትሪ

   የኮንጎ ኢንዱስትሪ ምርቶች እጅግ ውስኖች ናቸው፡፡ ከኮንጎ የኢንዱስትሪ መርቶች ውስጥ ቢራ፣ ስሚንቶ፣ የታሸጉ መግቦችና ከአልኮል ነፃ የሆኑ የታሸጉ መጠጦች አንዲሁም አረበ ብረት፣ ጨርቃጨርቅና የመኪና ጎማዎች ይገኛሉ፡፡ ኮንጎ ድሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ነፃነቷን ካገኘችበት ጊዜ  ጅመሮ ሀገሪቱ ለኢንዱስትሪ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቷን ቀጥላለች፡፡

 

የውጭ ንግድ

   ኮንጎ ወደውጭ ከምትልካቸው የሀገሪቱ ምርቶች መዳብ የመጀመሪያውን ቦታ ይይዛል፡፡ ከሌሎች ወደውጭ ከሚላኩ ምርቶች መካከል ኮፓልት፣ ቡና፣ ሰው ሰራሽ አልማዝና የዘምባባ ዘይት ይካተታሉ፡፡ ኮንጎ የተላዩ የምግብ ዓይነቶች፣ የነዳጅ ዘይት፣ ጨርቃጨርቅና የተፈበረኩ እቃዎችን ከውጭ ታስገባለች፡፡ የኮንጎ የውጭ ንግድ  በዋናነት የሚካሄደው ከምዕራብ አውሮባ ጋር ሲሆን በልጀየም የመጀመሪያውን ደረጃ ትይዛለች፡፡

 

የኮንጎ ድሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ቶሪዝም

የኮንጎ ወንዝ

 

ከኮንጎ የቶሪስት መስህብ ክልች በመጀመሪያ ደረጃ የሚጠቀሰው ዝናን ያተረፈውና ቶሪስቶች በሰፊው የሚጎበኙት የኮንጎ ወንዝ ነው፡፡ የውጭ ቶሪሰቶችም ኮንጎን በሚጎበኙበት ወቅት ለዚህ ወንዝ ልዩ ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ ይህን ወንዝ ከሌሎች ክልሎች ለየት የሜያደርገው አስደናቂ የተፈጥሮ ገጽታው፣ ተመልካችን የሚያስደስተው ማራኪ ትእይንቱና ለጽጥታ አፍቃሪዎች ተስማሚ መሆኑ ነው፡፡ ይህ በደቡባዊ ኮንጎ የሚገኘውና በአለም አቀፍ ደረጃ በእርዝመት ሁለተኛውን ቦታ ይዞ የሚገኘው የኮንጎ ወንዝ የውጭ ቶሪስቶች ወደሀገሪቱ እንዲያመሩ ከሚያደርጉ ክልሎች በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል፡፡

እሳተ ጋሞራ የኒራጆንጎ  “ Nirajongo volcano

 ይህ የሳተጋሞራ ክልል በኮንጎ ካሉ የቶሪስት መስህብ አካባቢዎች አንደኛው ሲሆን እሳተጋሞራው በሚነሳበት ወቅት ፎቶ ግራፎችን ለማንሳት በሺዎች የሚቆጠሩ የውጭ ቶሪስቶች ሀገሪቱን እንዲጎበኙ እድርጓል፡፡ ይህ እሳተጋሞራ -ፊሮንጋ - በመባል በሚታወቀው አጅግ አበይት ከሚባሉ የኮንጎ ፓርኮች አንዱ በሆነው ፓርክ ማእከላዊ ክፍል ይገኛል፡፡ ይህ የእሳተጋሞራ ክልል ዝናውን ያተረፈው በአፍሪካ ካሉ በሰፊው ከሚነሱ እሳተጋሞራዎች አንዱ ከመሆኑ  አንፃር ነው ፡፡

 

የሳሎንጋ ብሄራዊ ፓርክ   Salonga National Park  

 

ይህ ፓርክ አንደዝንጀሮ፣ ዘሆንና ቀጭኔ ያሉ የተላያዩ የዱር አራዊት እንደሁም እንደገነት ወፍ፣ የቦኖቦ ዝንጅሮ የሳሎንጋ ዝንጀሮ ያሉ ከምድረ ገጽ የመሰወር አደጋ የተደቀነባቸውን አራዊቶችን አእዋፍን ያከተተ በመሆኑ የኮንጎን የተሪሰት ቁጥር ከፍ በማደረግ ረገድ ልዩ ሚና እንዳለው ይነገራል፡፡

 ጠቀሜታው ከፍተኛ በመሆኑም ዩኒስኮ በአለም ከማይዳሰሱ ቅርሶች አንዱ ለመሆኑ እውቅና ስጥቶታል፡፡

የሊቪንግስቶን ፏፏቴ     Livingstone Falls

 የተለያዩ የተራራ ሰንሰሎቶችና ሸንተረሮች የሚያካትተው የሊቪንግስቶን ፏፏቴ በኮንጎ ካሉ መርጥ የቶሪስት መስህብ ክልሎች አንዱ ነው፡፡ ይህው በኃያልነቱና ተምዘግዛጊነቱ በአለም ካሉ ሕያው ፏፏቴዎች አንዱ የሆነው የሊቪንግስቶን ፏፏቴ በኮንጎ ወንዝ ግርጌ ይገኛል፡፡