በግብፅ 167 አዳዲስ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተመዘገበ ሲሆን አጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ወደ 51612 ከፍ ብሎል ።
እሑድ ፣ ነሐሴ 9 ቀን 2020
በግብፅ 167 አዳዲስ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተመዘገበ ሲሆን አጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ወደ 51612 ከፍ ብሎል ።

በግብፅ 167 አዳዲስ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተመዘገበ ሲሆን አጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ወደ 51612 ከፍ ብሎል ።

የግብፅ የጤና ሚኒስትር ቢሮ በትናንትናው ዕለት ቅዳሜ በ8/8/2020 በአለም አቀፍ የጤና ድርጅት  መመሪያ  መሰረት 1119  ሰዎች አስፈላጊው ህክምና ከተደረገላቸው በሆላ አገግመዉ  ከሆስፒታል የወጡ መሆናቸውን የገለፀ ሲሆን ።እስከ ትናትናው ዕለት ድረስ አጠቃላይ ከሆስፒታል አገግመው የወጡ ግለሰቦች ቁጥር ወደ 51612 ከፍ ብሎል፡፡ የግብፅ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሚዲያ ክፍል አማካሪ እና ቃል አቀባይ የሆኑት ዶክተር ካሊድ ሙጃሂድ እንዳስታወቁት ከሆነ 167 አዳዲስ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል እንድሁም 21 ሰዎች ሞተዋል፡፡ እስከ ቅዳሜ  ዕለት በኮሮና ቫይረስ 95314  ሰዎች ሲያዙ ከእነዚህም ውስጥ 51612  ሰዎች ከበሽታው ሲያገግሙ 4992  ሰዎች መሞታቸዉ ተመዝግቦል ::