ብሩንዲ
ብሩንዲ

የግብፅና የቡሩንዲ ግንኙ

ግብጽ ቡሩንዲ እ.ኤ.አ. በ1962 ነፃነቷን ካገኘች በኋላ ከሀገሪቱ ጋር የደፕሎማት ግንኙነት የመሰረተችና በ1964 ኢምባሲ የከፈተች የመጀመሪያዋ የአረብና ሙስሊም አገር ነበረች፡፡ ቡሩንዲ ግብጽ በአፍሪካ አንፃር የምትጫወተውን ሚና ታደንቃለች፡፡  እንዲሁም ከዐሥራ ሁለት አመት በላይ ባሰቆጠረው የቡሩንዲ የእርስ በርስ ጦርነትም እንኳን ሳያቋርጥ የቀጠለውን የግብጽን ድጋፍ ታመሰግናለች፡፡ የቡሩንዲው ወገን ከግብጽ ጋር ያለው ግንኙነት እንዲጠናከር በተለያዩ ዘርፎች የግብጽን ተሞክሮ ወጤት ወደሀገሪቱ ለማስገባት እንዲቻል ጥሪ ያቀርባል፡፡ የቡሩንዲው መሪ ፕሬዝዳንት ፒየር እንኩሮ እንዜዛ በጤናና በትምህርት ዘርፍ ግብጽ የምታደርገውን የቀጠለ ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

የሁለቱ አገራት ዋና ዋና የጉብኝት ልውውጥ፡:

እ.ኤ.አ. በ4/2/2019 የቡሩንዲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  ኢዚክያላ እንቤጌራ  በግብጽ የሥራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን የሀገሪቱ መሪ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታሕ አልሲሲ  ተቀብለው ያነጋገሯቸው ሲሆን ለቡሩንዲው መሪ ባሰተላለፉት የቃል መልእክት ከሁለቱ አገሮች ባለዉ የጋራ ግንኙነት ግብጽ የምትኮራ መሆኗን አመልክተው የጋራ ትብብሩን ለማጠናከርም ሀገራቸው ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል፡፡ የቡሩንዲው ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር የአገሪቱን መሪ የቃል መልእክት ባስተላለፉበት ወቅት በሁሉም ዘርፍ በተለይም ደግሞ በኢኮኖሚና በፖለቲካ መስኮች ያለው የሁለቱ አገራት ትብብር እጅግ ጠንካራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዚያን ወቅት ሸብርና ጽንፈኝነት አደጋን መከላከልና የአፍሪካን ሰላምና ደህነት ለማጠናከር የጋራ ስራውም በቅንጅት መሆን የሚሉትን ጉዳዮች ጨምሮ የሁለቱ አገራት አመለካከት ተመሳሳይ እንደነበረ ገልጸዋል፡፡

በ27/9/2018 የቡሩንዲው ህግ መወሰኛ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሚኒስቴር ሬቬርያን እንዲኮርቢዮ በግብጽ የሥራ ጉበኝት ባደረጉበት ወቅት በግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳይ ኃላፊ አምባሳደር ሐምዲ ሰነድ ሎዛ ጋር ተገናኝተው የሁለቱን አገራት ግንኙነትና ትብብር በማስቀደም በርካታ ጉዳዮችን ከመምከራቸውም ባሻገር የአባ ተፋሰስ አገሮችን ልማት እውን ማድረግ የሚቻለበትን መንገድ የመከሩ መሆኑ ታውቋል፡፡

በ18/4/2018 የቡሩንዲ ብሄራዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሚስተር ፈሀሰካለንያቢንዳ  በግብጽ የሥራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት የግብጹ የተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ኮክተር አሊ አብደል ኣል ጋር ተገናኝተው በሀገራቱ ሁለገብ ትብብር ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት አደርገዋል፡፡

በ16/5/2017 የግብጹ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳሚህ ሽኩሪ በቡሩንዲ ባደረጉት የሥራ ጉብኝት ከቡሩንዲው መሪ ፕሬዝዳንት ፕየር እንኮሮ እንዜዛ ጋር ተገናኝተው የሁለቱን አገራት ትብብር የመከሩ ሲሆን የሁለቱን አገራት ሁለገብ ትብብር እንዲሁም አህጉራዊና አለም አቀፍ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከፕሬዝዳንት አብደል ፈታሕ አልሲሲ የተላከ የቃል መልእክት አድርሰዋል፡፡ በ16/5/2017 የቡሩንዲ ቤተመንግሰት ጥበቃ ክፍል ኃላፊ ጀኔራል ኤልዲፎንሰ ሃባሮ ሪማ በግብጽ የሥራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ከሀገሪቱ መሪ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታሕ አልሲሲ ጋር ተገናኝተው ከመወያየታቸውም ባሻጋር የሁለቱን አገራት ሁለገብ ትብብር በተመለከተ ከቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ፔየር እንኮሮ እንዜዛ የተላከ የጽሑፍ ደብዳቤ ለፕሬዝዳንት አልሲሲ አድርሰዋል፡፡


የሁለቱ አገራት የኢኮኖሚ ትብብር፡

የግብጽና የቡሩንዲ የንግድ ልውውጥ ሁለገብ የምግብ ዓይነቶችን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ እንዲሁም የግንባታ ግብኣቶች በተለይም በቡሩንዲ የመልሶ ግንባታ ጊዜ የሲሚንቶና ሴራሚክ ምርቶች ቀደምትነት ነበራቸው፡፡ እንደ መድሃኒት፣ ማዳበሪያ፣ የፕላስቲክ ምርቶች፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ የቤት ቁሳቁስ ያሉትም ምርቶች በሁለቱ አገራት የንግድ ልውውጥ ይካተታሉ፡፡

የውሉ ማእቀፍ እንዲሚከተለው ሰፍሯል፡፡ 

አንደኛ፡ የተፈረሙ ውሎች፡፡

በ1973 የባህልና የስነ ጥበብ ስምምነት

1973 የአየር ትራንስፖርት ትብብር ስምምነት

1986 የኢኮኖሚና የቴክኒክ ትብብር ስምምነት

1988 የኢንዱስትሪ ዘርፍ የትብብር ፕሮቶኮል

1991 የቴሌቨዥን ስርጭት ዘርፍ ትብብር ፕሮቶኮል

በ1992 የንግድ ልውውጥ ስምምነት

በ2005 የግብጽ የአፍሪካ ጋር የቴክኒክ ትብብር ፈንድና የቡሩንዲ መንግስት ስምምነት

በ2008 የአል አዝሃር አልሸሪፍና የበሩንዲ የስላምና እርቅ ዩኒቨርስቲ ስምምነት

 

ሁለተኛ፡ በሁለቱ አገራት የጋራ ኮሚቴ 5ኛ ዙር ስብሰባ የተፈረመ ስምምነት

ከ2007 አስከ 2009 የተከናወኑ የባህል የሳይንስ፣ የቴክኒክና የሚዲያ ትብብር ፕሮግራሞች

ማህበራዊ ዘርፍ ትብብር የመግባቢያ ስምነት

የአሌክሳንድሪያ ቤተመፅሀፍትና ከቡሩንዲ ብሄራዊ ሬድዮና ቴሌቭዢን ስርጭት ትብብር የመግባቢያ ስምምነት

ከግብጽ አጠቃላይ የቤተ መፅሀፍትና ማህደራት ኮርፖሬሽንና ከቡሩንዲ ብሄራዊ መፅሀፍት ቤት አርካይቨ ማእክል የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት

የግብጽና የቡሩንዲ ብሔራዊ የጤና ማእከላት የትብብር ፕሮቶኮል

ሦስተኛ፡ ማርች 2009 በስድስተኛ ዙር የሁለቱ አገራት የጋራ ኮሚቴ ስብሰባ የተፈረሙ ውሎች፡፡ የሁለቱ አገራት የሲቪል ደህንነት ትብብር ውል

የግብጽ ብሄራዊ ባንክ ከቡሩንዲው አቻው ጋር የፈረመው የትብብር ውል፡፡

አራተኛ፡ በ2010 የተፈረሙ ውሎች

በ2010 የቡሩንዲ እርሻና የአሳ ሃብት ሚኒስቴር በካይሮ የሥራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት የተፈረመው የእርሻ፣ የእንሰሳት እርባታና የአሳ ማስገር የመግባቢያ ስምምነት

የግብጽ ኢንቨስትመንትና የነፃ ንግድ ቀጠና ድርጅት ከቡሩንዲው የቦጆምቦራ የኢንቨስትመንት ኮርፖሬሺን ጋር በጁላይ 6/2010 የፈረመው ውል፡፡

የሁለቱ አገራት የቴክኒክ ዘርፍ ትብብር፡

በ13/1/2017 ከግብጽ የኤሌክትሪክና የታዳሽ ሃይል ምንጭ ሚኒስቴር የተውጣጡ በርካታ መሃንዲሶችንና ቴክኒሻኖችን ያካተተ አንድ የግብፅ ልኡካን በቡሩንዲ የስራ ጉብኝትአድርጓል፡፡ ቡድኑ በዚህ ጉብኝት የቡሩንዲ ዋና ከተማ ቦጆምቦራ የኤሌክትሪክ ኃይል ማዞሪያዎችን አቅምና ብቃት እየተዘዋወረ የገመገመ ሲሆን ከዚያ በፊት ከአገልግሎት ውጭ ሆነው የነበሩ 10 የኤሌክትሪክ ሃይል ማዞሪያዎችን ጠግኖ እንደገና ለአግልግሎት እንዲበቁ ለማደረግ ያደረገው ሙከራ የተሳካ እንደነበርም ታውቋል፡፡