የግብፅእና የታንዛንያ ግንኙነቶች
የግብፅእና የታንዛንያ ግንኙነቶች

መግቢያ

በግብፅ እና በታንዛንያ  መካከል ያሉት ግንኙነቶች በደህንነት፤ በመከላከያ፤ በፓለቲካ፤በምጣኔሀብት፤ በማህበራዊ ዘርፎች እንዲሁም በተጨማሪ በፓለቲካዉ መድረክ፤በአለማቀፋዊ ትብብር፤ ሰብአዊ መብትን በማስከበር በአፍሪካ አህጉር አንድነትና ልማትን ለማረጋገጥ በመግባባትና ትብብርን መሰረትያደረገነዉ፡፡ በሁለቱ አገራት ታሪካዊ መሪወች አብደልናስርና ኔሪሪ ጊዜ ያስተሳሰረዉ ጠንካራ የፓለቲካ ግንኙነቶች ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት መመስረት የበኩሉን እገዛአድርጎል፡፡

የሁለቱ አገራት ታሪካዊ ዉርስን መሰረት በማድረግ የአሁኑ የአገራቱ መሪዎች የአፍሪካ ህብረት ልማት ሂደትንለማጠናከር፣በፓለቲካዉ ዘርፍ ሁለቱ አገራት በዋነኛነት በምስራቅ አፍሪካ አጀንዳዎች ይሰራሉ፡፤ታንዛኒያ ከአባይ ተፋሳስ አገራት አንዷ በመሆኗ በሁለቱ ወንድማማች አገራት መካከል ጠንካራ ትብብር አለ በሁለቱ አገራት መካከል አጠቃላይ ትብብሩን ለማጠናከር የአገራቱ ከፍተኛ የጋራ ኮሚቴ በየጊዜዉ ስብሰባ ያደርጋሉ፡፡

   የጉብኝት ልዉዉጦች እና ግንኙነቶች 

እ.ኤ.አ.በ4/11/2018 በታንዛንያ ገበያ የግብፅ ኢንዱስትሪዎችን ለማስተዋወቅ ምክንያት በማድረግ የግብፅ ኢንዱስትሪዎች ማህበር ልኡካን በማህበሩ የአፍሪካ ትብብር ኮሚቴ ሊቀመንበር ዶክተር ሸሪፍ አል ጀበሊ የበላይ መሪነት ከ24 የግብፅ ኩባንያ የተለያዩ ሴክተር የምጣኔ ሀብት ዘርፎች የተሳተፉበት ሰላሳ ተወካዮች በታንዛንያ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ልኡካኑንም የታንዛንያ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኦጀስቲን ማሂጃ የኢንዱስትሪዎች ማህበር ዳይሬክተር የኢንቨስትመንት ማእከል ዳይሬክተር የግል ሴክተር ድርጅት ዳይሬክተር የእርሻ፤የኢንዱስትሪ፤የንግድም/ቤትሊቀመንበር፤እንዲሁም በርካታ የግል ሴክተር ተወካዮች ተቀብለዋቸዋል፡፡

እ.ኤ.አ.በ8/1/2018 በዋነኛነት የታንዛንያ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኦጀስቲን ማሂጃ በዛንዚባር ፕሬዝዳንት ቢሮ የአገር ሚኒስቴር ኢሳ ሃጂ ኦሲን ያካተተዉ  ከፍተኛ ባለስልጣናት ልኡካን በግብፅ የስራጉብኝት አካሂደዋል፡፡የግብፅ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳሚህ ሽኩሪ ልኡካኑን ተቀብለዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ14/8/2017 የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ በታንዛኒያ ጉብኝት አድርገዋል ይህ ጉብኝት ለግብፁ ፕሬዝዳንት ከ1968 ጀምሮ የጀመሪያ ነዉ በዛን ወቅት የታንዛኒያዉ ፕሬዝዳንት ጆን ማጆ ፎሊ ተቀብለዋቸዋል:: ሁለቱ ወገናትም በበርካታ ቀጠናዊ ጉዳዮች መክረዉ በሁለቱ አገራት መካከል የጋራ ችግሮችን ለመታደግ በወታደራዊዉ እና በደህንነት ትብብር ማድረጉ ወሳኝ ነዉ በማለት አረጋግጠዋል፡፡ በአባይ ተፋሳስ አገራት ልማትን ገቢራዊ ለማድረግም ተወያይተዋል፡፡በሁለቱ አገራት መካከል ሙስናን ለመታደግ የዘርፍ ትብብሩን ለማጠናከር እና የአገራቱ የጋራ ኮሚቴ በቅርብ ጊዜ ተገናኝተዉ እንዲወያዩ እንዲሁም የሁለቱ አገራት ህዝቦችን የጋራ ጥቅም የሚያረጋግጥ ትብብርን ለማጠናከር የሁለቱ አገራት መሪዎች ተስማምተዋል፡፡እ.ኤ.አ በጃንዋሪ  31 2017 በአዲስ አበባ በተካሄደዉ የአፍሪካ ጉባኤ ጎን ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ ከፕሬዝዳንት ጆን ማጆ ፎሊ ጋር  ተገናኝተዉ ሁለቱ አገራትን የሚያገናኘዉ ታሪካዊ ግንኙነቶች ናቸዉ በማለት አረጋግጠዋል፡፡በተለያዩ መስኮች በሁለቱ አገራት መካከል ያለዉን ግንኙነት ለማጠናከር ፕሬዝዳንት አል ሲሲ ለታንዛኒያ አቻቸዉ በካይሮ ጉብኝት እንዲያደርጉ ጥሪ አድርገዋል፡፡ግብፅ በአፍሪካ የመሪነት ሚናዋ መመለሷን የታንዛኒያዉ ፕሬዝዳንት አወድሰዋል፡፡

 እ.ኤ.አ በ8/12/2016 የግብፁ የዉሀ ሀብት እና መስኖ ሚኒስቴር ዶክ. ሙሀመድ አብዱ አልአጢ በታንዛኒያ የስራ ጉብኝት አካሂደዋል፡፡የታንዛኒያዉ  የዉሀ  እና የመስኖ ሚኒስቴሩ ጄርሶን ሎየንጂ ተቀብለዋቸዉ በሁለቱ አገራት መካከል የጋራ ትብብሩን ለማጠናከር የሚቻልበትን ሁኔታ በተመለከተ ተወያይተዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ6/11/2015 የግብፁ የመሬት ልማት እና እርሻ ሚኒስቴር ዶክ.ኡሳም ፋይድ በታንዛንያ የፕሬዝዳንት ጆን ቦምቤ ጆዜፍ ማጆፎሊ የሹመት ዝግጅት በታንዛንያ ጉብኝት አድርገዋል፡፡የታንዛንያዉ ፕሬዝዳንት ህዝባቸዉን በሚመሩበት ወቅት ስራቸዉ ለዕድገት እና ለብልፅግና ስኬታማ እና ዉጤታማ እንዲሆን የፕሬዝዳንት አል ሲሲ የመንግስት እና የህዝባቸዉ ምኞት መሆኑን ፋይድ ለፕሬዝዳንቱ አስተላልፈዋል፡፡

  እ.ኤ.አ በ23/12/2014 የታንዛኒያዉ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በርናርድ ሜምቢ በግብፅ የስራ ጉብኝት አድርገዋል የግብፁ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳሚህ ሽኩሪ ተቀብለዋቸዉ ሁለቱ ወገናት በወሳኝ የዓለም ዓቀፋዊ እና ቀጠናዊ እንዲሁም በሁለትዮሽ ግንኙነቶች በጋራ መክረዋል፡፡ 

  እ.ኤ.አ በ8/6/2014 የታንዛንያ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በርናርድ ሜምቢ ለግብፁ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ በተካሄደዉ የሹመት ዝግጅት ለመሳተፍ የአገራቸዉን ልዑካን በመምራት በግብፅ ጉብኝት አካሂደዋል፡፡ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነቢል ፈህሚ ጋር ተገናኝተዉ በግብፅ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከተካሄደ በኃላ ግብፅ በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ዉስጥ ተሳትፎዋን እንድትቀጥል ተወያይተዋል፡፡የታንዛንያዉ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ግብፅ በአፍሪካ  ህብረት  ኮሚሽን የምታካሂደዉን ታሪካዊ ተሳትፎ ለማከናወን መመለሷን አወድሰዋል፡፡ ሁለቱ ወገናትም በአፍሪካ ጉዳዮች ቀጠናዊ ትብብሩን ለማጎልበት በተለይም በአፍሪካ አህጉር ልማትን ገቢራዊ ለማድረግ በአፍሪካ አህጉር የልማትን አሳሳቢነት የልማቱን ሂደት ለማከናወን ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እንዲሁም የአባይ ተፋሳስ አገራት ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የግብፅ ዉሀ አሳሳቢ መሆኑን ተረድተዉ የአንቴቢን ስምምነት በድጋሚ በጋራ እንዲወያዩበት ልዩ የታንዛኒያ ኢንሼቲቭን ተወያይተዋል፡፡

 እ.ኤ.አ በ25/4/2014  የቀድሞዉ  የግብፅ  ጠ/ሚኒስቴር  ኢብራሂም መህለብ በታንዛኒያ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት በርካታ የታንዛኒያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ተቀብለዋቸዋል፡፡ ጠ/ሚኒስቴሩም በግብፅ እና በታንዛኒያ መካከል የሁለትዮሽ ግንኝነቶች መክረዋል፡፡ የታንዛኒያዉ ፕሬዝዳንት ጃኪያ ኪኮይት ለቀድሞዉ ፕፌዝዳንት አድሊ መንሱር በ50ኛዉ የታንዛኒያ አንድነት በዓል እንዲገኙ ጥሪ አድርገዋል፡፡ ጠ/ሚኒስቴር መህለብም ፕሬዝዳንት አድሊ መንሱርን ወክለዉ የአፍሪካ አገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና መሪዎች በሚሳተፍበት በዚህ ታላቅ ዝግጅት ተሳትፈዋል ፡፡ ግብፅም ከአፍሪካ አገራት ጋር ያላትን ግነኙነት ለማጠናከር ሁሉንም ዕድሎች ትጠቀማለች በታንዛኒያ ያደረጉት ጉብኝትም ይህን መሰረት ያደረገ ነዉ በማለት መህለብ አረጋግጠዋል፡፡

 የአል-አዝሀር አል-ሸሪፍ ተቋም መካከለኛዉን የእስላማዊ አስተምህሮ ለማስፋፋት በሚያደርገዉ አስተዋፅኦ በታንዛኒያ 1400 ታንዛኒያዊ ተማሪዎችን ያቀፈዉን የግብፅ እስላማዊ ማእከልን መህለብ ጎብኝተዋል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1968 ማዕከሉ ከተቋቋመበት ዕለት አንስቶ አል-አዝሀር በበላይነት የሚቆጣጠረዉ ሲሆን ግብፅም የማዕከሉን ሙሉ ወጭ ትሸፍናለች ፡፡ ማዕከሉም በየዓመቱ 20 ተማሪዎችን በአል-አዝሀር አልሸሪፍ ትምህርታቸዉን እንዲቀጥሉ ወደ ግብፅ ይልካል፡፡

እ.ኤ.አ. በ22/2/2014 የግብፅ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በታንዛኒያ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ ከታንዛኒያዉ ፕሬዝዳንት ጃካያ ኪኮዮት ጋር ተገናኝተዉ ግብፅ ከታንዛኒያ ጋር በተለያዩ መስኮች በፖለቲካ፣በምጣኔሀብት፣በንግድ፣በወታደራዊ ዘርፎች የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ለማጠናከር እና በአጠቃላይ በአፍሪካ አህጉር ወቅታዊ ጉዳዮች እንዲሁም በተጨማሪ ከአፍሪካ ህብረት ጋር ስላለዉ ግንኙነት የግብፅን ራዕይ ከፕሬዝዳንት አድሊ መንሱር የተላከዉን መልዕክት ለፕሬዝዳንት ኪኮዮት አድርሰዋል፡፡

 እ.ኤ.አ. በጃንዋሪ 2003 ፕሬዝዳንት ቤንያሚን በግብፅ ጉብኝት አድርገዋል ፡፡ ከቀድሞዉ ፕሬዝዳንት ሙባረክ ጋር ተገናኝተዉ በበርካታ የአፍሪካ ጉዳዮች፣ በሁለትዮሽ ግንኙነቶች፣በአፍሪካ ልማትን ለማጠናከር፣ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲሁም በዓለም ዓቀፋዊ እና በቀጠናዊ ጉዳዮች በጋር መክረዋል፡፡

 እ.ኤ.አ. በጁላይ ወር 2003 የታንዛኒያዉ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከግብፅ የዉጭ ንግድ ሚኒስቴር ጋር የንግድ ትብብር እና ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት በሁለቱ አገራት መካከል ነፃ የንግድ ቀጠና እንዲቋቋም ተስማምተዋል፡፡

 እ.ኤ.አ. በዲሰምበር 2003 በታንዛኒያ መዲና ዳረ-አልሰላም በተካሄደዉ የአፍሪካ ኤግዚቢሽን ግብፅ ተሳትፋለች፡፡

እ.ኤ.አ. በኦክቶበር 2002 በግብፅ የባለሀብቶች ማህበር እና በታንዛንያ የእርሻ የኢንዱስትሪ የንግድሚኒስቴር መካከል የግብፅ ታንዛኒያ የሰራተኞች ምክር ቤት ለማቋቋም ስምምነት አካሂደዋል፡፡ በሁለቱ አገራት መካከል ከጉምሩክ ነፃ ለመለዋወጥ ልዩ ስምምነትን ተወያይተዋል፡፡ ይኸዉም እንደኮሜሳ ስምምነት የጉምሩኮች ዉሳኔን ከሁለቱ ወገናት በኩል ሸቀጦች ላይ የጉምሩክ ቅነሳን የሚያደርግ ነዉ፡፡በስዊዝ ካናል ድርጅት እና ኩባንያዉ እንዲሁም በዳረሰላም ወደብ መካከል ትብብር ለማድረግ እንዲሁም በአሌክሳንድሪያ የአረብ አካዳሚ የባህርትራንስፖርት የስልጠና ፕሮግራሞችን ለማከናወን ተወያይተዋል፡፡

 እ.ኤ.አ. በጁላይ 16 2001 በታንዛያ ዳረ አል-ሰላም በተካሄደዉ 24ኛ ዙር ኤግዚቢሽን የግብፅ ክፍል ልዩ ሽልማትን አግኝቶል ፡፡ በኤግዚብሽኑ የቀረቡ የግብፅ ምርቶች የቤት ቁሳቁስ፣ሴራሚክ፣የምግብ ዉጤቶች፣የጥጥ ምርቶች፣የኻን ኸሊል ምርቶችን ያካተተ ነዉ፡፡

 እ.ኤ.አ. በማርች 2000 የግብፅ የኢንቨስትመንት ድርጅት በሁለቱ አገራት መካከል የጋራ ፕሮጀክቶችን ለማቋቋም በግንባር ቀደምትነት በእርሻ፣በማዕድን፣በምግብ ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም በታንዛኒያ ኢንዱስትሪ ተፈላጊ የሆኑ የቴክኒክ ባለሙያዎችን በማሰልጠን እና ታንዛንያን በግብፅ ቴክኖሎጂ ለማገዝ ጥናት አድርጎል፡፡

 እ.ኤ.አ. በጁላይ 1999 ፕሬዝዳንት መካባ በግብፅ የስራ ጉብኝት አድርገዋል ከቀድሞዉ ፕሬዝዳንት ሙባረክ ጋር ተገናኝተዉ ታንዛንያ ባለችበት የገበያ ኢኮኖሚ እና የመንግስት ሴክተርን የግል ለማድረግ ባለችበት ሁኔታ በበርካታ የምጣኔ ሀብት ጉዳዮች መክረዋል፡፡ ፕሬዝዳንት መካባም በአል-አሸር ረመዳን መዲና በተመለከቱት የግብፅ ኢንዱስትሪ እና ቴክኖሎጂ ብልፅግና ተገርመዋል ፡፡ የሁለቱ አገራት ከፍተኛ የጋራ ኮሚቴ በሁለቱ አገራት የግል ሴክተር መካከል ትብብሩን ለማበረታታት ኮሚቴዉ እንዲያተኩር እና የቀረጥ ሂደት ማሻሻያን በተመለከተ የምጣኔሀብት ግንኙነቶች የፖለቲካ ግንኙነቶችን ከፍ የሚያደርግ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ ሁለቱ አገራትም ተጨማሪ ስምምነቶችን የሚሹ አይደሉም እ.ኤ.አ በ1977 የተፈረሙ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ከለላ ስምምነቶችን ገቢራዊ ማድረግ ይሻሉ ስምምነቶቹን ገቢራዊ ለማድረግ ባለሀብቶች ከፍተኛ ሚና አላቸዉ በማለት ፕሬዝዳንት መካባ አረጋግጠዋል፡፡

  የምጣኔ ሀብት ስምምነቶች

እ.ኤ.አ በ9/1/2018 የግብፅ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳሚህ ሽኩሪ በሁለቱ አገራት መካከል በከፍተኛ ባለስልጣናት የተጀመረዉን  የጋራ ሚኒስቴሮች ኮሚቴ ሶስተኛ ዙር ስብሰባ መርተዋል፡፡ ኮሚቴዉም በሁለቱ ወገናት መካከል በሁለትዮሽ ትብብር እና በቀጠናዊ ጉዳዩች በጋራ መክሮል ፡፡ በመጨረሻም የጋራ ኮሚቴዉ በዲፕሎማሲ፣በቱሪዝም፣በእርሻ የስልጠና ዘርፎች ሶስት የመግባቢያ ስምምነቶችን ፈርሞል፡፡

  ስምምነቶች

 እ.ኤ.አ. በ1996 በሮማ በተካሄደዉ ዓለምዓቀፋዊ የምግብ ጉባኤ ኮንፈረንስ አላማዎችን የምግብ ዋስትና ፖለቲካን ለማበረታታት እ.ኤ.አ. በሜይ 1999 በታንዛኒያ፣በግብፅ እና በFAO ድርጅት የምግብ ዋስትና ልዩ ፕሮግራምን ገቢራዊ ለማድረግ ስምምነት አካሂደዋል፡፡

  በጤና ጥበቃ ዘርፍ ትብብር

በአሌክሳንድሪያ እና በሞሀምቢሊ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የሳይንስ እና የጤናዉን ትብብር ለማበረታታት የተካሄደዉን ስምምነት መሰረት በማድረግ እ.ኤ.አ በ17/8/2016 ከአሌክሳንድሪያ ዩኒቨርሲቲ 7 ሀኪሞችን ያካተተዉ ልዑካን የህፃናት የቀዶ ጥገና ህክምና ለማካሄድ በታንዛኒያ እና በዛንዚባር ደሴት የስራ ጉብኝት አካሂደዋል ፡፡ ከአሌክሳንድሪያ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ልዑካን የስራ ጉብኝት ሲያደርግ ለሶስተኛ ዓመት በተከታታይ ሶስተኛ ጊዜ ነዉ ፡፡ የህክምና ልዑካኑም እ.ኤ.አ በ2014 2015 አስቸኳይ የህክምና ዕርዳታ የሚፈልጉ ህፃናትን ለማከም እና የቀዶ ጥገና ህክምን ለማካሄድ በታንዛንያ የስራ ጉብኝት አካሂደዋል፡፡

  ዕርዳታ

በሰሜን ታንዛኒያ በካጂራ አካባቢ በተከሰተዉ ርዕደ-መሬት ለተጎዱት እ.ኤ.አ. በ8/12/2016 ግብፅ ዕርዳታዎችን ልካለች፡፡ ዕርዳታዉም ከ4.5 ቶን በላይ የሚደርስ በርካታ የህክምና መድሀኒት እና ቁሳቁሶች እንዲሁም መኖርያ ቤታቸዉ ለተጎዳ መጠለያን ጭምር ያካተተ ነዉ፡፡ የዕርዳታዉም ወጭ 70 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ፈጅቶል ዕርዳታዉን በታንዛኒያ ጠ/ሚኒስቴር ቢሮ ተወካይ ከፍተኛ ባለስልጣናት ተረክበዋል፡፡