የግብፅ እና ቶጎ ግንኙነቶች
የግብፅ እና ቶጎ ግንኙነቶች

   አጠር ያለ ታሪካዊ መግለጫ

በግብጽ እና  በቶጎ መካከል የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች የተጀመረው ቶጎ እ.ኤ.አ በ1960 ነጻነቱዋን ካገኘች በኃላ ነበር ፡፡ ከዛን ጊዚ ጀምሮ በቶጎ የግብጽ ኢምባሲ ነበር፡፡ በዛን ወቅትም በካይሮ የቶጎ ኢምባሲ አልነበረም ፡፡

ቶጎም እ.ኤ.አ በ2004 መጨረሻ በሊቢያ የሚገኘውን የቶጎ አምባሳደር በግብጽ በጊዚያዊነት ቶጎን እንዲወክል እጩ አድርጋ አቀረበች የግብጽ ባለስልጣናትም በነገሩ ተሰማሙ፡፡ ሁለቱ አገራትም በፖለቲካው ዘርፍ ያላቸው ግንኙነቶች  ጠንካራ ነው፡፡ በአለምአቀፋዊ እና በቀጠናዊ ጉዳዮች ያላቸው ሀሳብ ተመሳሳይ ነው፡፡ በተጨማሪም ቶጎ የግብጽን ጥቅም የሚጎዳ ፖለቲካ አታካሂድም፡፡ በአለም አቀፋዊ እና በቀጠናዊ ድርጅቶች እንዲሁም ዝግጅቶች ለሚቀርቡ ግብጽዉያን እጩዎች ቶጎ ድጋፍ ታደርጋለች ፡፡

 የጉብኝቶች ልዉዉጥ

 እ.ኤ.አ በ10/4/2016 የቶጎዉ ፕሬዝዳንት ፎር ጀናሰንጀቢ በግብጽ ጉብኝት አድርገዋል ፡፡   የግብጽ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ ተቀብለዋቸዉ ሁለቱ ወገናት የሁለቱ አገራትን ህዝቦች ጥቅም ገቢራዊ ለማድረግ በሁሉም መስኮች የሁለትዮሽ  ግንኙነቶችን ለማጠናከር የሚቻልበትን ሁኔታ በማስመልከት ተወያይተዋል ፡፡ በተጨማሪም በአለምአቀፋዊ  እና በአፍሪካዊ የጋራ አሳሳቢ ጉዳዮች እንዲሁም በአፍሪካ አህጉር አሸባሪ እና ድህነትን ለመታደግ እንዲሁም የምጣኔ ሀብት እና የማህበራዊ ልማትን ለመደጎም ተወያይተዋል ፡፡

እ.ኤ.አ በ4/3/2016 የቶጎዉ ፕሬዝዳንት ፎር ጀናሲንጀቢ ለግብጽ ባደረጉትጥሪ ግብዣ መሠረት የግብጽ ብሐራዊ የብሮጀክቶች እስትራቴጅያዊ የግብጽ ፕሬዝዳንት ረዳት የሆኑት መሀንዲስ መህለብ በቶጎ የስራ ጉብኝት አካሂደዋል ፡፡ በዚሁ ጉብኝታቸውም ከፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ ለቶጎው አቻቸው የተላከውን መልእክት አድርሰዋል ፡፡ ሁለቱ ወገናትም በበርካታ መስኮች የጋራ ትብብሩን ለማጠናከር በባህር፤ በትራንስፖርት፤ በአየርመንገድ ፤ በጤና ፤ በእርሻ፤ በሀይል ማመንጫ፤ በመኖሪያቤቶች፤ በቱሪዝም ዘርፎች ተወያይተዋል፡፡

 እ.ኤ.አ በ2016 በግብጵ ሸርምሸህ ከተማ በሚካሄደው የአፍሪካ ፎረም ለመሳተፍ የቶጎ ጠ/ሚኒስቴር ኮሚ ሰይሉም ክላስ በ21/2/2016 በግብጵ ጉብኝት አድርገዋል ፡፡ በዚህ ወቅትም ከፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ጋር ተገናኝተው የሁለትዮሽን ትብብር ለማጠናከር ተወያይተዋል ፡፡ የፕሬዝዳንት ፎር የፓለቲካ አማካሪ እና የቀድሞው የቶጎ ውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር ኮፊ ኢሳሳው እ.ኤ.አ በ2009 ከጁላይ 13-14 በሸርምሸህ ከተማ ለሚካሄደው የገለልተኛ አገራት ጉባኤ የሚኒስቴሮች ቅድመዝግጅት ኮንፈረንስ ተሳትፈዋል፡፡

የቶጎ የቱሪዝም ሚኒሰቴር እ.ኤ.አ በ2009 በማርች ወር በግብጵ ባደረጉት የሥራ ጉብኝት ከግብጵ የቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር ተገናኝተው በሁለቱ አገራት መካከል የቱሪዝም የጋራ ትብብርን ለማጠናከር የመግባቢያ ስምምነት አካሂደዋል ፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 ከሜይ 31 እስጀ ጁን 2 በግብጵ መዲና ካይሮ በተካሄደው የአፍሪካ የኢነርጂ ሚኒስቴሮች ሶስተኛ ፎረም ኮንፈረንሰ የቶጎ የኢነርጂ እና የማእድን ሚኒስቴር በዚሁ ኮንፈረንስ ተሳትፈዋል ፡፡ ከፕሬዝዳንት ኣያዲማ ሞተ ህልፈት በኃላ በቶጎ ያለውን ፓለቲካዊ ችግር ለመፍታት እ.ኤ.አ በ21/2/2005 የፕሬዝዳንት የፖለቲካ አማካሪ በግብጵ የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

እ.ኤ.አ ከ2-4/11/2007 የአፍሪካ ህብረት ጉዳይ እና በውጭ ጉዳይ የአፍሪካ ጉዳይ ረዳት ሚኒስቴር በቶጎ የስራ ጉብኝት አድርገው ከቶጎው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና ፀሀፊ እና ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር ተገናኝተዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2008 በጁላይ ወር ፕሬዝዳንት ፎር በግብፅ ሸርም ሸህ ከተማ በተካሄደው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ለመሳተፍ በግብፅ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

 እ.ኤ.አ ከኦክቶበር 21-23 2010 በአፍሪካ ህብረት ጉዳይ እና በውጭ ጉዳይ የአፍሪካ ጉዳይ ረዳት ሚኒስቴር በቶጎ የስራ ጉብኝት አድርገው ከቶጎው ጠ/ሚኒስቴር ፤ ከከፍተኛ ፍርድ ቤት ሊቀመንበር ፤ከፓርላማ ም/ሊቀመንበር ፤ ከጤና ጥበቃ ፤ ከቱሪዝም፤ከደህንነት ሚኒስቴሮች ጋር በቶጎ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተገናኝተው በሁለቱ አገራት መካከል ያሉትን የሁለትዮሽ ግንኙነቶች ለማጠናከር እንዲሁም በምእራብ አፍሪካ ቀጠና ያሉትን ሁኔታወች የሁለቱ አገራትን አቀሞች በተመለከተ የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል፡፡

የምጣኔ ሀብት ግንኙነቶች

 

 

እ.ኤ.አ በ19/2/2017 በግብጽና በቶጎ መካከል በአየር ደህንነት፤ሰላም፤ ጥራት የሰልጠና ዘርፎች በግብጽ የሲቪል አቪዮሽን ሚኒስቴር ሸሪፍ ፈትሂ እና በቶጎ  የትራንሰፖርት ሚኒስቴር የ መግባቢያ ስምምነት አካሂደዋል ፡፡

እ.ኤ.አ በ10/4/2016 የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ እና የቶጎው ፕሬዝዳንትፎር ጀናሲንጀቢ በሁለቱ አገራት በተካሄደዉ የፕሮቶኮል እና አራት የጋራ ትብብር ፕሮግራሞች ስምምነት ዝግጅት ተገኝተዋል፡፡                                                                                                                                     

በሁለቱ አገራት የተካሄደው የፕሮቶኮል ስምምነት በመኖሪያ ቤት እና ህንፃ ዘርፎች ሲሆን ከግብጽ በኩል ሰምምነት የፈረሙት  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳሚ ሽኩረ ሲሆኑ ከቶጎ  በኩል የመኖሪያቤት እና የከተማ ፕላን ሚኒስቴር ካቦ ሲስኖ ናቸው  ፡፡ ሁለቱ ወገናትም አራት የትብብር ማሰፈፀሚያ ፕሮግራሞችን ፈርመዋል፡፡እነዚህም እንደሚከተሉት ናቸው፡፡

በስፖርት ዘርፍ በግብፅ የወጣቶች የስፖርት የማስታዎቂያ ሚኒስቴር በኩል እና በቶጎ የወጣቶች የስፖርት የባህል የማስታወቅያ ሚኒስቴር መካከል የትብብር አፈጻጸም ፕሮግራም  ከግብጽ በኩል ስምምነቱን የፈረሙት የወጣቶች እና የስፖርት ሚኒስቴር ካሊድ አብዱልአዚዝ  ከቶጎ በኩል የወጣች ፤ የስፖርት የባህል የማስታወቂያ ሚኒስቴር ናቸው፡፡

በባህሉ ዘርፍ በግብጽ የባህል ሚኒስቴር እና በቶጎ የወጣቶች የስፖርት የባህል የማሰታዎቂያ ሚኒስቴር መካከል የትብብር አፈፃፀም ፕሮግራም ከግብጽ በኩል የፈረሙት የባህል ሚኒስቴር ሂልሚ አል-ነሚም ከቶጎ በኩል የወጣቶች የስፖርት የባህል የማስታወቅያ ሚኒስቴር ናቸው፡፡

በማስታወቅያው ዘርፍ በግብፅ የመንግስት መረጃ አገልግሎት እና በቶጎ የባህል ወኪል መካከል የትብብር አፈፃፀም ፕሮግራም ከግብፅ በኩል የፈረሙት የመንግስት የመረጃ አገልግሎት ሊቀመንበር አምባሳደር ሰላህ አብዱልሳዲቅ ከቶጎ በኩል የወጣቶች የስፖርት የባህል የማስታወቅያ ሚኒስቴር ናቸዉ፡፡

በሬድዮ እና ቴሌቨዥን ዘርፍ በግብፅ ሬድዮ እና ቴሌቨዥን ማህበር እና በቶጎ የወጣቶች የስፖርት የባህል የማስታወቅያ ሚኒስቴር መካከል ከግብፅ በኩል የፈረሙት የሬድዮ እና ቴሌቨዥን ማኅበር ሊቀመንበር ኡሳም አል-አሚር ከቶጎ በኩልየወጣቶች የስፖርት የባህል የማስታወቅያ ሚኒስቴር ናቸዉ፡፡

አል ነስር አስመጭ እና ላኪ ኩባንያ እንደ ሶስተኛ ወገን ወደ አዉሮፓ የሚላኩ  ለቶጎ የእርሻ ምርቶችን እንደ ቡና፤ ካካዉ ትልካለች፡፡

የጋራ ኮሚቴ

እ.ኤ.አ በፌብሪዋሪ ወር 1988 በሁለቱ አገራት መካከል የጋራ ኮሚቴ ተቋቋቀመ፡፡

እ.ኤ.አ በፌብሪዋሪ ወር 1988 በካይሮ  የመጀመሪያዉ ስብሰባ ተካሄደ፡፡

እ.ኤ.አ በጥር ወር 1999 በሎሚ ሁለተኛዉ ስብሰባ ተካሄደ፡፡

       በሁለቱ አገራት የጋራ ኮሚቴ መካከል የተካሄዱ ስምምነቶች

እ.ኤ.አ በ17/3/1964 የተፈረመው የባህል ትብብር  ስምምነት በ1991 1992 1993 የአፋፃፀም ፕሮቶኮል ስምምነት ተካሂዶል፡፡

እ.ኤ.አ በ17/3/1964 የንግድ ትብብር ስምምነት ተካሂዶል፡፡

እ.ኤ.አ በጃንዋሪ 27 1981 የምጣኔሀብት እና የቴክኒካዊ ትብብር ስምምነት ተካሂዶል፡፡

እ.ኤ.አ በ18/4/1981 የወታደራዊ ትብብር የፕሮቶኮል ስምምነት

እ.ኤ.አ በ6/2/1988 ከአፍሪካ ጋር የቴክኒካዊ ትብብር ለማድረግ ከግብፅ ተቀም ጋር የቴክኒካዊ የትብበር ስምምነት ተካሂዶል፡፡

እ.ኤ.አ በ 6/2/1988 በባህር ትራንስፖርት የተፈረመ ስምምነት፡፡

እ.ኤ.አ በ26/3/2009 በቱሪዝም ዘርፍ ትብብር ለማድረግ የተካሄደ የመግባባያ ስምምነት፡፡             በሁለቱ አገራት መካከል የባህላዊ እና የቴክኒካዊ ግንኙነቶች

በቶጎ በተለያዩ /ሀገራት በሚገኙ እስላማዊ /ቤቶች በእስላማዊ አስተምህሮ  በአረብኛ ቋንቋ፤በቅዱስ ቁርአን ዘርፎችየሚያስተምሩ የአል-አዝሀር ልኡካን በቶጎ ይገኛሉ፡፡ አል-አዝሀርም በተቋሞቹ ለቶጎ ተማሪዎች በየአመቱ ነፃ የትምህርት አድልን ይሰጣል፡፡

የግብፅ የጋራ ልማት ድርጅት በበርካታ የተለያዩ ዘርፎች በሚያዘጋጀዉ እንደ የፖሊስ እርሻ ዳኝነት ህክምና ነርሲንግ ሚድያ ድፕሎማሲያዊ የስልጠና ኮርሶች በየጊዜዉ ለቶጎ ጥሪ ያደርጋል፡፡ እንደዚሁም የመድሃኒት የህክምና ቁሳቁሶችን የሎጂስቲክ ድጋፍ እርዳታ ያደርጋል፡፡