ቻድ

የግብፅ እና የቻድ ግንኙነቶች

በመንግስትም ሆነ በህዝብ ደረጃ የግብፅ እና የቻድ ግንኙነቶች እጅግ ጠንካራ ናቸዉ፡፡ የግብጽ አብዮት እ.ኤ.አ በ1952 ከተካሄደ በኋላ ግብፅ በአፍሪካ ያላትን ከፍተኛ ሚናና ቦታ መሰረት በማድረግ ቻድ ከግብፅ ጋር ያሏትን ግንኙነቶች በልዩ መልክ አጠናክራለች፡፡ ቻድ ለግብፅ ብሔራዊ ደህንነት ወሳኝ አገር እንደ መሆኖ የግብፅ እና የቻድ ግንኙነት ሰፊ ነዉ:: ከሱዳን እና ከሊቢያ ጋር የጋራ የድንበር ወሰን አሏት፡፡ የቻድን ታሪክ ወደኋላ መለስ ብለን ስንመለከተው ስር መሰረቱ ከንጉሰ ነገስታት ዘመን ጋር የተያየዘ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡