የግብፅ እና የቻድ ግንኙነቶች
የግብፅ እና የቻድ ግንኙነቶች

ግብፅ እና ቻድ

በመንግስትም ሆነ በህዝብ ደረጃ የግብፅ እና የቻድ ግንኙነቶች እጅግ ጠንካራ ናቸዉ፡፡ የግብጽ አብዮት እ.ኤ.አ በ1952 ከተካሄደ ኋላ ግብፅ በአፍሪካ ያላትን ከፍተኛ ሚናና ቦታ መሰረት በማድረግ ቻድ ከግብፅ ጋር ያሏትን ግንኙነቶች በልዩ መልክ አጠናክራለች፡፡ ቻድ ለግብፅ ብሔራዊ ደህንነት ወሳኝ አገር እንደመሆኖ የግብፅ እና የቻድ ግንኙነት ሰፊ ነዉ:: ከሱዳን እና ከሊቢያ ጋር የጋራ የድንበር ወሰን አሏት፡፡ የቻድታሪክ ወደኋላ መለስ ብለን ስንመለከተው ስር መሰረቱ ከንጉሰ ነገስታት ዘመን ጋር የተያየዘ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ በሁለተኛዉ ዓመተ ሂጅራ ወይም በስምንተኛዉ ምዕተ ዓመት በቻድ የመጀመርያ እስላማዊ አረባዊ ንጉሳዊ አገዛዝ በተመሰረተበት ወቅት የሰሜን ምስራቅ ሀይቅ ስም ካኒም ነበር፡፡ ከዛም በሶስተኛዉ ዓመተ ሂጅራ እስከ መሀከለኛዉ ሱዳን አካባቢ ቻድ ለመስፋፋት ችላ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ ከ1920 ጀምሮ እ.ኤ.አ በ1960 ነፃነቶን እስከ አገኘችበት ጊዜ ድረስ በፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ስር ነበረች፡፡

የጉብኝት ልዉዉጥ

. እ.ኤ.አ በኦገስት 2017 ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ በቻድ የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

.  እ.ኤ.አ በ16/10/2018 የፕሬዝዳንቱ ልዩ ልዑክ የሆኑት የግብፅ ፕሬዝዳንት ብሔራዊ ፕሮጀክትና እስትራቴጂያዊ ረዳት መሀንዲስ ሸሪፍ ኢስማኤል በቻድ የስራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት በቻድ የዓለም ዓቀፍ ትብብርና የአፍሪካ ዉህደትና የዉጭ ጉዳይ ዋና ፀሀፊ አሽታ ሷሊህ ዳሞኒ አቀባበል አድርገዉላቸዋል፡፡ ከቻድ የነዳጅ ሚኒስቴር ኢስማኤል ጋርም ተገናኝተዋል፡፡

. እ.ኤ.አ በዲሰምበር 2014 የቻዱ ፕሬዝዳንት እድሪስ ዴቢ በግብፅ የስራ ጉብኝት አድርገዉ በጤንነት እና በእርሻ ዘርፎች የትብብር መግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

. እ.ኤ.አ በአፕረል 2014 የቀድሞዉ ጠ/ሚኒስቴር በቻድ ባደረጉት የስራ ጉብኝት በእርሻዉ ዘርፍ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

የንግድ ልዉዉጥ

 

በፔትሮሊየም ዘርፍ፡ ቻድ በሚያስፈልጋት በፔትሮሊየም ሴክተር የሚሰሩ የቻድ ባለሙያዎችን ብቃት ከፍ ለማድረግ ግብፃዉያን ባለሙያዎች ስልጠና እንዲሰጡ ሁለቱ ወገናት ተስማምተዋል፡፡

በቱሪዝም ዘርፍ፡ ከቻድ በቀረበዉ የትብብር ስምምነት ፕሮጀክት ጥናት በፍጥነት ለማካሄድ ሁለቱ ወገናት ተስማምተዋል፡፡

በንግድ ዘርፍ፡ ሁለቱ አገራት በኤግዚቢሽኖች እና በዓለም ዓቀፋዊ ገበያዎች ለመሳተፍ ከግብፅ በኩል ለቻዱ አቻዉ የመግባቢያ ስምምነት ፕሮጀክትን አቅርቧል፡፡

. የአረብ ኮንትራክተር በቻድ በስፋት ይሰራል፡፡

የባህል እና የትምህርት ግንኙነቶች

ከአፍሪካ አገራት በርካታ የአል-አዝሀር አል ሸሪፍ ልዑካን (40 ልዑካን) በቻድ ይገኛሉ ፡፡ የአል-አዝሀር ተቋምም ትምህርቱን በበላይነት ይቆጣጠራል፡፡  አል-አዝሀርም በሁለተኛ ደረጃም ይሁን በዩኒቨርስቲ ነፃ  የትምህርት ዕድል ይሰጣል፡፡ ቻድ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ በርካታ ነፃ የትምህርት ዕድል ታገኛለች፡፡

በቻድ የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጥያቄ መሰረት የትምህርታዊ ድርጅቶችን ድጋፍ ለማድረግ ከግብፅ ዩኒቨርሲቲዎች ሶስት ፕሮፌሰሮች እጩ ሆነዋል፡፡