የግብፅ እና የኡጋንዳ ግንኙነቶች
የግብፅ እና የኡጋንዳ ግንኙነቶች

የግብፅ እና የኡጋንዳ ግንኙነቶች

 የግብፅ -ኡጋንዳ ግንኙነቶችን ልዩ  የሚያደርገዉ  በበርካታ ዓለም ዓቀፋዊ ጉዳዮች በግብፅ እና በኡጋንዳ መካከል  ያሉት  የጋራ ሀሳቦች ናቸዉ ፡፡ በተጨማሪም  በሁለቱ አገራት መካከል በቀጠናዊ  ጉዳዮች ትብብር እና ትስስር በዋነኛነት የዉሀ ጉዳይ፣ አሸባሪን ለመታደግ እና የቀጠናዊ ጉዳዮች ይገኙበታል ፡፡

 እ.ኤ.አ በጁን  2014 ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ በትረ ስልጣኑን ከያዙበት ዕለት አንስቶ በሁለቱ አገራት  መካከል ያሉት  ግንኙነቶች  በአዎንታዊ መልኩ ተሻሽለዋል :: ባለፉት  ጊዚያትም  የግብፅ -ኡጋንዳ  ግንኙነቶች  ተጠናክረዉ ግብፅ  አፍሪካዊ  መሰረቷን  እንድትይዝ  አድርጓታል፡፡ ለዚህም  ፕሬዝዳንት  አል ሲሲ ግብፅ በአፍሪካ አህጉር የነበራትን ታሪካዊ ሚና እና መሪነቷን  እንድትይዝ  ለማድረግ  በአፍሪካ  ጉዳዮች እና ፎረሞች ተሳትፈዋል ፡፡ በግብፃዉያን  እና በአፍሪካዊያን  ባለስልጣናት  መካከል የጉብኝት ልዉዉጦች  ተካሂደዋል ፡፡

 እ.ኤ.አ  ከጁን 30 አብዮት  በኃላ  ግብፅ ወደ አፍሪካ  ህብረት እንድትመለስ ኡጋንዳ የአፍሪካ  የደህንነት እና የሰላም ምክርቤትን  በምትመራበት ወቅት ለግብፅ ድጋፍ በማድረግ ግልፅ  አቋም ወሰዳለች፡፡

ፕሬዝዳንት ዮሪ ሞሲፌኒ በግብፅ ባካሄዱት የስራ ጉብኝት ከፕሬዝዳንት  አል ሲሲ ጋር  የግብፅ እና የኡጋንዳ  ህዝቦችን የጋራ ጥቅም  መሰረት ያደረገ መርህን  በምጣኔ ሀብት፣በፖለቲካዊ፣ የተለያዩ ዘርፎች የጋራ እስትራቴጂን  ለማጠናከር ተወያይተዋል፡፡

የሁለቱ አገራት  ግንኙነቶች ግብፅ ከአፍሪካ አገራት እና ከአባይ ተፋሳሽ አገራት ጋር ላሉት ግንኙነቶች  የትብብር ዘርፎችን  ለማጠናከር በሁለቱ አገራት ባለስልጣናት  መካከል የጉብኝት  ልዉዉጦችም ይሁን በጋራ ኮሚቴዎች በኩል ዋና ተምሳሌት ነዉ፡፡ ግብፅም ወደ አፍሪካ  አህጉር  ማተኮሯ ከግብፅ የዉጭ  ዋና ፖለቲካ  ከሆኑት ዉስጥ አንዱ  ነዉ፡፡ በፕሬዝዳንት አል ሲሲ የስልጣን ጊዜ ግብፅ በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ነበረችበት ቦታ ተመልሳለች፡፡

ኡጋንዳ  አሸባሪዎችን ለመታደግ እንድትችል ግብፅ በፀረ- አሸባሪ ዘርፍ  ኡጋንዳዉያንን በማሰልጠን የምታደርገዉን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ኡጋንዳ አወድሳለች፡፡ በሁለቱ አገራት መካከል በደህንነት፣በመከላከያ ዘርፎች ትብብሩን ለማጠናከር ኡጋንዳ በግብፅ ታላላቅ የወታደራዊ ኮሌጅዎች ስልጠና የማግኘት ዕድል አግኝታለች፡፡

የጉብኝት ልዉዉጦች

በሁለቱ አገራት መካከል የሁለትዮሽ ጠንካራ ግንኙነቶች የጉብኝት ልዉዉጦች እንደሚከተሉት ናቸዉ፡፡

. ፕሬዝዳንት ዮሪ ሞሲፌኒ በካይሮ እ.ኤ.አ በ2018 ከግንቦት 8-9 ባደረጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ጎንዮሽ በሁለቱ አገራት መካከል ከፍተኛ  የጋራ ኮሚቴ በበርካታ ዘርፎች ለመተባበር የመግባቢያ ስምምነት አካሂደዋል፡፡

. ፕሬዝዳንት ሞሲፌኒ  እ.ኤ.አ በ2017 ጁን 22 የአባይ ተፋሳሽ አገራት መሪዎች የመጀመሪያ ጉባኤ በአንተቢ ባደረጉት ጥሪ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ተሳትፈዋል የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስቴር እና የአባይ ተፋሳሽ አገራት መሪ ተወካዮችም ተገኝተዋል፡፡

 .       ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ እ.ኤ.አ በ2016 ዲሰምበር  18 በኡጋንዳ ያደረጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ከፈርኦን ዘመን ጀምሮ የግብፅ ፕሬዝዳንት በኡጋንዳ የመጀመርያ የሁለትዮሽ ጉብኝት ነዉ በማለት ፕሬዝዳንት ሞሲፌኒ ገልፀዋል፡፡

.  የግብፅ መንግስት እርዳታ ከሚያደርገዉ አንዱ የሆነዉ እና የአረብ ኮንትራክተር ኩባንያ የሚሰራዉ በምዕራብ ኡጋንዳ በካሲሲ ክ/ሀገር የጎርፍ አደጋን የመታደግ ፕሮጀክት የመክፈቻ ስነ-ስርዐት ለመገኘት እ.ኤ.አ በ2017 ኦገስት የግብፅ የዉሀ ሀብት እና የመስኖ ሚኒስቴር ዶክተር ሙሀመድ አብዱል አጢ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል::

 .  የአባይ ተፋሳሽ አገራት ጉባኤ ዝግጅቶችን ለማከናወን  የግብፅ ዉጭ  ጉዳይ ሚኒስቴር ሳሚህ ሽኩሪ እ.ኤ.አ በ2017 ሜይ  በኡጋንዳ  ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዉ ከፕሬዝዳንት ዮሪ ሞሲፌኒ ጋር ተገናኝተዋል፡፡

.  እ.ኤ.አ በ2014 ጁን በፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ የሹመት ዝግጅት የኡጋንዳ የክልል ጉዳይ አስተዳደር ሚኒስቴር ተገኝተዋል፡፡

.  እ.ኤ.አ በ2014 ጁን ማላቦ በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ጉባኤ ጎንዮሽ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ ከኡጋንዳ  አቻቸዉ ዮሪ ሞሲፌኒ ጋር ተጋናኝተዋል ፡፡

.  እ.ኤ.አ በ2015 ጃንዋሪ የሁለቱ አገራት መሪዎች በአዲስ አበባ በተካሄደዉ የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ወቅት     ተገናኝተዋል፡፡

.  እ.ኤ.አ በፌብሪዋሪ 2015 የኡጋንዳ የአስተዳደር ቁጥጥር ልኡካን በካይሮ መዲና የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

.  እ.ኤ.አ በአፕሪል 2015 የኡጋንዳ የቱሪዝም ሚኒስቴር በግብፅ የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

.  እ.ኤ.አ በአፕሪል 2015 የግብፅ የዲፕሎማት ተቋም ልዑካን በኡጋንዳ የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

.  እ.ኤ.አ በሜይ 2015 የግብፅ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳሚህ ሽኩሪ በኡጋንዳ ባደረጉት የስራ ጉብኝት ከፕሬዝዳንቱ ጋር ተገናተዋል፡፡

.  እ.ኤ.አ በማርች 2015 የኡጋንዳ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  በካይሮ ባደረጉት የስራ ጉብኝት ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳሚህ ሽኩሪ ጋር ተገናኝተዋል፡፡

.  እ.ኤ.አ በጁን 2015 የግብፅ የደህንነት ልዑካን በኡጋንዳ የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

.  እ.ኤ.አ በኦገስት 2015 የኡጋንዳ  ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና ፀሀፊ ከግብፁ አቻቸዉ የአፍሪካ ጉዳይ ም/ሚኒስቴር የበላይ መሪነት በካይሮ የሁለትዮሽ ኮሚቴ ስብሰባ

.  እ.ኤ.አ በኦገስት 2015 የኡጋንዳ የአካባቢ እና የዉሀ ሚኒስቴር በአዲሱ የሲዊዝ ቦይ የመክፈቻ ስነ-ስርዐት ተገኝተዋል፡፡

.  እ.ኤ.አ በኦገስት 2015 የግብፅ የድጋፍ ም/ሚኒስቴር በኡጋንዳ የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

.  እ.ኤ.አ በኦክቶበር 2015 የግብፅ አስተዳደራዊ ቁጥጥር ቡድን ልኡካን በዋና ወኪል  የበላይ መሪነት በኡጋንዳ ስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

.  እ.ኤ.አ በዲሰምበር 2015 የግብፅ የመስኖ ሚኒስቴር በኡጋንዳ የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

.  የኡጋንዳ የመኖሪያ ቤቶች  ሚኒስቴር  በግብፅ  የስራ  ጉብኝት አድርገዋል፡፡

.  የኡጋንዳ የቀንድ ከብት  እና የገንዘብ ሚኒስቴሮች በግብፅ የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

.  የኡጋንዳ የደህንነት ሚኒስቴር  በግብፅ የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

.  እ.ኤ.አ  በአፕሪል 2016 የኡጋንዳ የዉጭ  ደህንነቶች ድርጅት ሊቀመንበር በካይሮ የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

. እ.ኤ.አ በሜይ 2016 የግብፅ ከፍተኛ ትምህርት እና የአገር ዉስጥ ልማት ሚኒስቴሮች በሞሴፊኒ የሹመት ዝግጅት ተገኝተዋል፡፡