የግብጽ እና ኢትዮጵያ ግንኙነቶች
የግብጽ እና ኢትዮጵያ ግንኙነቶች

የግብጽና ኢትዮጵያ ግንኙነት በአፍሪካ ታሪክ እጅግ የጠንት ከሚባሉት
ግንኙነቶች ይመደባል፡፡ የሁለቱ አገሮች ግንኙነት ወደ ኋላ መለስ ብልን
ስንመለከተው በወቅቱ የነበረውን የሁለቱን አገሮች የንግድ ልውውጥ ጉዞ
መሰረት አድረጎ በፎሮናዊያን ዘመን እንደተጀመረ እንረዳለን፡፡
የግብጽና ኢትዮጵያ የድፕሎማት ግንኙነት የተመሰረተው ደግሞ እ.ኤ.አ
አቆጣጠር በ 1927 ነበር፡፡ በመሆኑም በዓለምና በአፍሪካ ታሪክ እጅግ የጥንት
ከሚባሉት ግንኙነቶች አንዱ እንደሆነ ይነገርለታል፡፡
የድፕሎማት ግንኙነት

ይህ የሁለቱ አገሮች ግንኙነት፣ ሁለቱ አገሮች እንደ የአባይ ውሃ፣ የአፍሪካ
ቀንድ ደህንነት፣ የባህር ወሮበላ ወንጀልና የሸብር ተቃውሞ ትግል ባሉ ሕያው
ፋይሎች የሚጋሩ በመሆናቸው ልዩ ገፅታ ያለው ግንኙነት እንደሆነ ይነገርለታል፡፡
እንዲሁም ግብጽ፣ኢትዮጵያና ሱዳን ከለጋሽ አገሮች ጋር በመተባበር በውሃና
ኃይል ምንጭ ዘርፎች የሦስቱን አገሮች ጥረት በማቀናጀትና በመደጎም ረገድ
ይንቀሳቀስ የነበረው የምስራቅ አባይ ተፋስስ ቴክኒክ ቢሮ -ENTRO- አባል
አገራት ናቸው፡፡
ሁለቱ አገራት የመላ አባይ ተፋሰስ አገሮችን ትብብር ኢላማ አድርጎ በ1999
እ.ኤ.አ የተዋቀረውና በሰፊው የተፋሰሱን ህዝብ ፍላጎት አንዳረጋገጠ
የሚነገርለት የአባይ ተፋሰስ ኢኒሸቲቭ ማህበር አባል ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት
ደግሞ የህዳሴው ግድብ ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ አባል አገራት ናቸው፡፡
የግብጽና ኢትዮጵያ ግንኙነት የግብጹ መሪ ፕሬዝዳንት አብደልፈታሕ አልሲሲ
በጁን ወር 2014 በግብጽ በትረ ስልጣን ከያዙ በኋላ ጉልህ የሆነ አዎንታዊ
አድገት እንደታየበት ይነገራል፡፡
የግብጹ መሪ ፕሬዝዳት አብደልፈታሕ አልሲሲ በሐገሪቱ የስልጣን ርክክቡ
ወቅት በአሰሙት ነግግር የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከግብጽና ኢትዮጵያ መካከል
ለሚፈጠር ውዝግብ ምክኒያት እንዲሆን አልፈቅድም ማለታቸውና ይህን
ቃላቸውን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን በሰፊው ማስተጋባታቸው ከሁለቱ አገሮች
መካከል አዲስ የተባለ የመቃራረብ ዓይነት እንደተፈጠረ ይታመናል፡፡
ከዚያም በመቀጠል በ2018 እ.ኤ.አ ኤክዋቶሪያል ጊኒ በተካሄደው
የአፍሪካ ህብረት መደበኛ የመሪዎች ጉባኤ ፕሬዝዳት አልሲሲ በተሰተፉበት
ወቅት ከኢትዮጵያው ተቅላይ ሚኒስተር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር
ተገናኝተው ተወያዩ፡፡ በዚያን ወቅትም ሁለቱ መሪዎች ማንኛውም የተፋሰሱ
አባል አገር በሌላው የተፋሰሱ አባል አገር ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት ሳያደርስ
አገሩን የማልማት መብቱ የተጠበቀ መሆኑን የሚያረጋግጥ ባለ ሰባት ነጥብ

መግለጫ አወጡ፡፡ ይህም የሁለቱ አገሮች ግንኙነት እንዲጠናከር ተጨማሪ ሚና
ነበረው፡፡
የግብጽና የኢትዮጵያ ግንኙነት በአፕሪል 2018 አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ
ሚኒስተር ዶክተር አቤይ አሕመድ ገዢው የኢትዮጵያ ህዝቦች አቤወታዊ
ድሞክራሲያዊ ግንባር በአካሄደው የውስጥ ምርጫ አሸንፈው በኢትዮጵያ
ስልጣን ከተረከቡ ወዲህ ቀላል ነው የማይባል መሻሻል እንደታየበት
ተስተውሏል፡፡
የግብጹ መሪ ፕሬዝዳንት አብደልፈታሕ አሲሲ ባደረጉላቸው ጥሪ መሰረት
የኢትዮጵያው ጠቅላ ሚኒስተር ዶክተር አቤይ አሕመድ በካይሮ የሥራ ገብኝት
ካደረጉ በኋላ ሁለቱ አገሮች አዲስ የግንኙነት ምዕራፍ እንደጀመሩ ይታመናል፡፡
ከዚያም በኢትዮጵያ መዲና አዲስ አባባ የሚያደርጉት የግብጽ ተጣያቂዎች
የሥራ ጉብኝት ቀጠለ፡፡ የግብጹ ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ሳሚሕ ሹክሪና የሀገሪቱ
የድህንነት ኤጀንሲ የበላይ ተጠሪ ሌተና ጄኔራል አባስ ካሚል በኦገስት ወር
2018 በአዲስ አበባ በአደረጉት የሥራ ጉበኝት ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር
ዶከተር አቤይ አሕመድ ጋር ፍሪያማ ውይይት ከማድረጋቸውም ባሻገር የሁለቱን
አገሮች የጋራ ትብብር አስመልክቶ ከግብጹ መሪ ፕሬዝዳንት አብደልፈታሕ
አልሲሲ የተላከ የቃል መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

የኢኮኖሚ ዘርፍ ትብብር

የግብጽና ኢትዮጵያ የጋራ የኢኮኖሚ ትብብር ቀላል ግምት የሚሰጠው
አይደለም፡፡ ከአንድ በሊዮን ዶላር በላይ ካፒታል ያለው የሶወይዲ ኤሌክትሪክ
ኬብል ፋብሪካ የኢንቨስትመንት ፕሮጄክትን ጨምሮ በርካታ የግብጽ
የኢንቨስትመንት ፕሮጄዎች በኢትዮጵያ በሰፊው ተሰራጭተው ይገኛሉ፡፡ እንዲሁም
የግብጽ ጎልዴን ትሬድ፣ የመስኖ ግብኣቶች አምራች የግብጽና ኢትዮጵያ የውሃ
ፕሮጄና የጂዮ ስቴንቲክ ኩባንያ እንዲሁም የሥጋ ልማት ፕሮጄና በርካታ እርሻ
ተኮር ፕሮጄዎች የሁለቱን አገሮች የኢኮኖሚ ትብብር እያጠናከሩት ይገኛሉ፡፡
የጤና ዘርፍ ትብብር

የግብጽና የኢትዮጵያን የጤና ዘርፍ ትብብር ለማጠናከር ከ 2009 እ.ኤ.አ
ጀምሮ ግብጽ በተለያዩ ጊዚያት የጤና ብድን ልኡክ ወደ ኢትዮጵያ ትልካለች፡፡
ይህን ትብብር በበለጠ ለማጠናከር በግብጽ የሚገኘው 75375 የካንሰር
ህክምና ሆስፒታልና በኢትዮጵ ጤና ጥብቃ ስር የሚገኙት የጥቁር አንበሳና
የሳንጻውሎስ ሆስፒታሎች የጋራ ሥራ ስምምነት ተፈራርመው በመስራት ላይ
ይገኛሉ፡፡

እንዲሁም በሴፕተምንበር 2015 እ.ኤ.አ የግብጹ ጳጳስ አባ ቲዎድሮስ
ሦስተኛ በኢትዮጵያ የሥራ ጉብንት ባደረጉበት ወቅት የግብጽ የከፕቲክ
ቤተክርስቲያን ወጩን የሸፈነውን የግብጽና ከናዳ ሆሽፒታል አዲስ አበባ ውስጥ
መርቀው ከፍተዋል፡፡ በዚያን ወቅትም በዚሁ የተላያዩ የቀዶ ጥገና ህክምና
ወጭ መሸፈን ለማይችሉ ኢትዮጵያዊያን የነፃ አገልግሎት በሚሰጠው ሆስፒታል
ለሚሠሩ ነርሶችና የተላያዩ ዘርፎች ሠራተኞች 3000 የዩኒቮርም ልብስና 200
የመለያ ኬፖች በእርዳታ መልክ ተበርክተዋል፡፡
ይህንኑ ትብብር ለማጠናከር በርካታ የግብጽ የህክምና ባለሞያዎች በኢትዮጵያ
ሆስፒታሎች ከጊዜ ወደጊዜ የሥራ ጉበኝት ያደርጋሉ፡፡ እንዲሁም በርካታ
የኢትዮጵያ የህክምና ባለሞያዎች በግብጽ በሚካሄዱ የህክምና ዘርፍ ኮርሶች
ይሳተፋሉ፡፡ እንዲሁም በ2015 የግብጽ የጤና ጥብቃ በለንደን የሚኖሩ
የህክምና ባለሞያዎች በኢትዮጵያ በሚገኘው የግብጽና ካናዳ ሆስፒታል ልዩ ልዩ
ስልጠና እንዲሰጡ በማስተባበር በኩል ታላቅ ሚና ተጫውቷል፡፡
በአዲስ አባባ ለሚገኘው የግብጽና ካናዳ ሆስፒታል በዩ ኤስ አሜሪካ የሚገኙ
የኮፕቲክ እምነት ተከታዮች ያበረከቷቸው የኩላሊት ማጠቢያ ማሽኖች፣
ቴሌስኮፖችና ሌሎችም የህክምና መሳሪያዎች ይገኛሉ፡፡
በዩ ኤስ አሜሪካ የሚገኘው የጀርባ አጠንት -አከርካሪ- መታጠፍ ህመም
ህክምና ማህበር ኃላፊ ዶክተር ከማል ኢብራሂም ያሰተባበሩቻውና የመሯቸው
የተለያዩ የህክምና ብድን ልኡካን በተለያየ ጊዜ የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን
ያከናውናል፡፡
በ2017 እ.ኤ.አ. በዶክተር መጅዲ ያቆብ የተመራው የህክምና ቡድን
በኢትዮጵያ ባደረገው የሥራ ጉብኝት በጥቁር አንበሳና በበርካታ የኢትዮጵያ
ሆስፒታሎች ልዩ ልዩ የልብ ህመም ቀዶ ጥገና ህክምና አካሂዷል፡፡
አንዲሁም የኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያን ወጭውን የሽፈነውን ከአሜሪካና
አንግሊዝ የተወጣጡ በጎ ፈቃደኛ የህክምና ባለሙያዎችን ያከተተውና ወደ
አሥር የሚጠጉ ተንቀሳቃሽ ክሊኒኮች በርካታ የህክምና ማሽኖችና መድሃኒቶች
ያቀፈው የግብጽ የህክምና ጤና ቡድን ልኡክ በጥርስ፣በዓይንና በውስጥ ደዌ
ዘርፍ… በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞችና መንደሮች አየተዘዋወሩ የነፃ ህክምና
አገልግሎት ዓመቱን ሙሉ ይሰጣሉ፡፡
የግብጽ ጤና ጥበቃ በበኩሉ የነርቭ፣ የኢንፍሎይንዛ፣ የአጥንት፣ የአከርካሪ፣
የአንገት ህመም እንዲሁም የሌሎች ዘርፎች ባለሞያዎችን ያካተተ የህክምና
ቡድን በየ3 ወሩ ወደኢትዮጵያ ይልካል፡፡

የቤተ ክርስቲኖች ግንኙነት

ከግብጽ የኮፕቲክ ቤተ ክርሰቲያንና ከኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋህዶ ቤተ
ክርስቲያን መካከል ጠንከራ መንፈሳዊ ትስስር እንዳለ ይታወቃል፡፡ እስካለፈው
ክፍለ ዘመን አጋማሽ ድረስ የግብጽ ኮፕቲካዊ ቤተ ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳስ
የኢትዮጵያን ጳጳስ ቀብቶ የመሾም ደንብ የተለመደ ነበር፡፡ በግብጽ ካቴድራል ቤተ
ክርስቲያን ቋሚ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ተወካይ ቄስስ መኖሩ የሁለቱ ቤተ
ክርስቲያኖች ጠንከራ መንፈሳዊ ግንኙነት እንደገና መመለሱን ያረጋግጣል፡፡
የግብጽ ሊቃነ ጳጳስ አባ ቴዎድሮስ ሦስተኛ ከሴፕተምበር 26 አስከ 30
2015 እ.ኤ.አ በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉበኝት እጅግ ስኬታማ ብሎም ታሪካዊ
ጉብኝት እንደነበረ ተነግሮለታል፡፡ ጳጳሱ በዚያን ጊዜው የኢትዮጵያ ጉብኝታቸው
ወቅት በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል በአክሱም፣ በጎንደርና በላሊበላ ይፋዊ ገብኝት
ከማድረጋቸውም ባሻገር ለ5 ቀናት በዘለቀው የኢትዮጵያ ቁየታቸው በርከታ
እንቅስቃሲዎችን ያደረጉ ሲሆን የነዚህ እንቅስቃሴዎች ስኬትና መልካም
ውጤት -ከልዝብ የፖለቲካ መሳሪያ አንዱ የሆነችው- የግብጽ ቤተ ክርስቲያን
የግብጽን የውጭ ግንኙነት በመደጎም ረገድ ታላቅ ሚና የምትጫወት መሆኗን
በግልፅ ያሳያል ሲሉ ታዛቢዎችይግልፃሉ፡፡