ግብፅ እና ኮሞሮስ
ግብፅ እና ኮሞሮስ

ግብፅ እና ኮሞሮስ

ሁለቱ አገራት በእስላማዊ የትብብር ድርጅት፣ በአረብ ሊግ፣ በአፍርካ ህብረት ኮሚሽን  አባል አገራት እንደመሆናቸዉ ግብፅ እና ኮሞሮስ በሁሉም መስኮች ያሏቸው የሁለትዮሽ  ግንኙነቶች ጠንካራ ናቸዉ፡፡ የትምህርት እና የባህል ግንኙነቶች ጥልቅ ከመሆናቸዉም በላይ ለአያሌ ዘመናት በርካታ የኮሞሮስ ተማሪዎች በግብፅ ዩኒቨርሲቲዎችም ይሁን በአል-አዝሀር አል ሸሪፍ የትምህርት ተቋም ለመማር ወደ ግብፅ ይመጣሉ፡፡

የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተቀጥላ የሆነዉ ለአፍሪካ ልማት የግብፅ  አጋርነት ድርጅት አማካኝነት ግብፅ  በተለያዩ መስኮች ለኮሞሮስ ባለሙያዎች የቴክኒክ ድጋፍ ታደርጋለች፡፡ ኮሞሮስም በሁሉም የዓለም ዓቀፋዊ፣ የአረባዊ፣ የአፍሪካዊ መድረኮች ለግብፅ ድጋፍ ታደርጋለች ፡፡

የግብፅ እና የኮሞሮስ ሪፐብሊክ የዲፕሎማት ግንኙነት የተጀመረዉ ግብፅ ከኮሞሮስ ጋር የዲፕሎማት ለዉዉጥ ለማድረግ እ.ኤ.አ በጁላይ 26 -1976  በወሰነችበት ወቅት ነበር፡፡ሁለቱ አገራትም በተለያዩ መስኮች የትብብር ልዉዉጡን ለማጠናከር ጥረት ከማድረጋቸዉም በላይ በበርካታ ዓለም ዓቀፋዊ ድርጅቶች ለምሳሌ፡ በአረብ ሊግ፣ በእስላማዊ ኮንፈረንስ ድርጅት፣ በዓለም ዓቀፋዊ የፍራንክፎን ድርጅት፣በአፍሪካ ህብረት በጋራ ከመጎዳኘታቸዉም በተጨማሪ የአፍሪካዊ የምጣኔ ሀብት ቡድን ዋና ምሰሶ በሆነዉ የኮሜሳ አባል ከሆኑ በኃላ በምጣኔ ሀብት ዘርፍ የጋራ ግንኙነቶችን ለማጠናከር በስፋት ሰርተዋል፡፡

የፖለቲካ ግንኙነቶች

በሁሉም መስኮች ያሉትን ግንኙነቶች ለማጠናከር ብሎም ለማሻሻል በሁለቱ አገራት ባለስልጣናት መካከል የጉብኝት ልዉዉጦችን በማከናወን በበርካታ የአፍሪካ አህጉር እና የቀጠናዊ ጉዳዮች የሁለቱ አገራት ራዕይ የሚስማማ ነዉ፡፡

የወታደራዊ ግንኙነቶች

እ.ኤ.አ ከ1997-1999 በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስር በኮሞሮስ ሰላምን ለማሰፈን በተደረገዉ ጥረት ግብፅ ሶስት ወታደራዊ ተቆጣጣሪዎችን በማሰለፍ ድጋፍ አድርጋለች፡፡