ደቡብ አፍሪካ

ግብፅ እና ደቡብ አፍሪካ

• ግብጽ ከረዢም ጊዜ በፊት ከቅኝ ግዛት ጋር የብዙ ዓመታት ትግል አካሂዳለች፡፡ ነፃነቷን ከተጎናጸፈች በኋላ ደግሞ በአፍሪካ የሚካሄዱ የነፃነት ንቅናቄዎችን በመደገፍ ግልጽ አቋም ነበራት፡፡ ከዚያም በደቡብ አፍሪካ የነበረውን የዘር መድሎ ስርኣት ወደሚቃወመው አለም አቀፍ ስርኣት ተቀላቀለች፡፡ በደቡብ አፍሪካ የነበረው የዘር መድሎ አስተዳደር ከተወገደና በሀገሪቱ የመጀመሪያው የብሄራዊ አንዲነት መንግስት እ.ኤ.አ. በ1994 ከተመሰረተ በኋላ ነገ ዛሬ ሳትል የድፕሎማት ግንኙነት መስርታ ከሀገሪቱ ጋር የሁለገብ ትብብር ስምምነትም ተፈራርማለች፡፡