ግብፅ እና ደቡብ አፍሪካ
ግብፅ እና ደቡብ አፍሪካ

 

ግብፅ እና ደቡብ አፍሪካ

ግብጽ ከረዢም ጊዜ በፊት ከቅኝ ግዛት ጋር የብዙ ዓመታት ትግል አካሂዳለች፡፡ ነፃነቷን ከተጎናጸፈች በኋላ ደግሞ በአፍሪካ የሚካሄዱ የነፃነት ንቅናቄዎችን በመደገፍ ግልጽ አቋም ነበራት፡፡ ከዚያም በደቡብ አፍሪካ የነበረውን የዘር መድሎ ስርኣት ወደሚቃወመው አለም አቀፍ ስርኣት ተቀላቀለች፡፡ በደቡብ አፍሪካ የነበረው የዘር መድሎ አስተዳደር ከተወገደና በሀገሪቱ የመጀመሪያው የብሄራዊ አንዲነት መንግስት እ.ኤ.አ. በ1994 ከተመሰረተ በኋላ ነገ ዛሬ ሳትል የድፕሎማት ግንኙነት መስርታ ከሀገሪቱ ጋር የሁለገብ ትብብር ስምምነትም ተፈራርማለች፡፡ ግብጽ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ከፍተኛ ጥረት የምታደረገው ሁለቱ አገራት በደቡብና ሰሜን አፍሪካ ተወዳዳሪ የሌለው የምለከዓ ምድር አቀማመጥ ያለቸው በመሁኑ የአፍሪካን ጉዳዮች ለመደጎም መሆኑን ትገልጻለች፡፡ ሁለቱ አገራት ክብደት፣ አቅምና ችሎታም በአህጉራዊም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ ጉለህ ሚና ለመጫወት የሚችሉ ከመሁኑ አንፃርም እንደሆነ ትጠቁማለች፡

የሁለቱ አገራት የፖለቲካ ግንኙነት

 • የሁለቱ አገራት የፖለቲካ ግንኙነት በአሁኑ ወቅት ቀላል የማይባል እምርታ እያስመዘገበ መሆኑ ይነገራል፡፡ የዚህ ዓይነቱ እድገት የጀመረው የሁለቱ አገራት መሪዎች ኒው ዮርክ ውስጥ 2014 በተካሄደው ጉባኤ ጎንዮሽ በአደረጉት ወይይት ነበር፡፡ ከዚያም የቀድሞው ደቡብ አፍሪካ መሪ ፕሬዝዳት ጃኮብ ዞማ የግብጹ አቻቸው ፕሬዝዳንት አብደልፈታሕ አልሲሲ ባደረጉላቸው ጥሪ መሰረት በእፕሪል ወር 2015 በግብጽ ያደረጉት ጉብኝት፣ ከዚያም በኋላ የሆለቱ አገራት መሪዎች ራሻ በሁለተኛው የኣለም ጦርነት በናዚያዊያን ላይ የተቀዳጀውን የድል 70ኛ አመት በአከበረችበት ወቅት ሞስኮ ውስጥ ተገናኝተው ያደረጉት የጎንዮሽ ወይይት ለሁለቱ አገራት የድፕሎማት ግንኙነት አድገት ተጨማሪ አስተዋጽኦ ነበራቸው፡፡
 • የቀድሞው የግብጽ ጠቅላይ ሚኒስተር እንጂነር ኢብራሂም ሚሕሊብ እ.ኢ.አ. በጁን 2015 ጁሃንስበርግ ውስጥ በተካሄደው 25ኛ ዙር የአፍረሪካ ህብረት መደበኛ ጉባኤ ሀገራቸውን በመወከል ተሳትፈዋል፡፡ እንዲሁም በዚያው አመት ደሴምበር ውስጥ በተካሄደው የአፍሮ ቻይና ጉባኤ የቀድሞው የግብጽ ጠቅላይ ሚኒስተር እንጂነር ሸሪፍ ኢስማኢል ተሳትፈዋል፡፡ በዚያው አመት ደቡብ አፍሪካ በተካሄደው አለም አቀፍ የኢኮኖሚ ጉባኤ የሀገሪቱን መሪ ፕሬዝዳንት አብደልፈታሕ አለሲሲን በመወከል የግብጹዋ አለም አቀፍ ትብብር ሚኒስተር ወ/ሮ ሰሐር ነስር ተሳትፈዋል፡፡
 • የግብጹ ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ከደቡብ አፍሪካዋ አቻቸው ጋር በተለያዩ ቦታዎች በርካታ ውይይቶችን አካሄደዋል፡፡ ከነሱም መካከል ሴፕተምበር 2014 ኒውርክ ውስጥ በተካሄደው 70ኛ ዙር የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ወቅት ያደረጉት የጎንዮሽ ውይይት፣ ኦክቶበር 12 2015 ካይሮ ውስጥ በተካሄደው የጋዛ መልሶ ግንባታ ጉባኤ ወቅት ያደረጉት ሰብሰባ፣ በአፕሪል2015 የቀድሞው ደቡብ አፍሪካ መሪ ጃኮብ ዞማ በካይሮ በአደጉት የሥራ ጉብኝት ወቅት ያደረጉት ወይይት፣ በ2015ቱ የጁሃንስበርግ የአፍሪካ ህብረት መደበኛ የመሬዎች ጉባኤና በዚው ዓመት አዚያው ጁሃንስበርግ በተካሄደው የአፍሮ ቻይና ትብብር የመሪዎች ጉባኤ ወቅት ያደረጉት የጎንዮሽ ሰብሰባ ይገኙበታል፡፡
 • እ.ኤ.አ. በ2015 ፕሪቶሪያ ከዚያ በፊት በሁለቱ አገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስተሮች መሪነት ፕሪቶሪያ ውስጥ ተካሂዶ የተቋረጠው የሁለቱ አገራት የጋራ ኮሚቴ ስብሰባ እንደገና እንዲቀጥል ያላትን ፍላጎት ገለጸች፡፡ ከዚያም የደቡብ አፍሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከግብጽ እምባሲና ጉዳዩ ከሞመለከተው ክፍል ጋር ለጋራ ኮሚቴው ስብሰባ ቅደመ ዝግጅት ጀመረ፡፡ የደቡብ አፍሪካ መንግሰት በ2016 ውስጥ ለጋራ ኮሚቴው የስብሰባ ቀን ተስማሚ ጊዜ እንዲወሰን ያለውን ፍላጎት ገለጸ፡፡ አንዲሁም በዚያ ዓመት 2016 አጋማሽ የጋራ ንግድ ኮሚቴው እንዲካሄደም ሃሳብ አቀረበ፡፡
 • አ.ኤ.አ. በ2014ና በ2015 በርካታ የግብጽ ልኡካን በደቡብ አፍሪካ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በቀደምትነት የሚጠቀሱት በአፕሪል የቀደሞው የግብጽ ሳይንሳዊ ምርምር ሚኒስተር እ.ኤ.አ. በ2015 በፕሪቶሪያ ያደረጉት ጉብኝት፣ እንዲሁም በዚያው በ2015 የግብጽ መንግስት የጥሩ ምርት ማእከል ልኡክ የግብጽ ኢንዱስትሪ ፌደሬሽን ልኡክ በፕሪቶሪያ የሥራ ጉብኝት አደርገዋል፡፡ በ2014 ደግሞ የግብጽ ከፍተኛ የምርጫ ኮሚቴ፣ የፍትህ ሚኒስትር፣ የሲቪል ማሀበረሰብ ልኡካን በፕሪቶሪያ ጉበኝት አደርገዋል፡፡ በቅርቡ ደግሞ ሴፕተምበር 2018 የግበጹ ብሄራዊ የምርጫ ምክር ቤት በነፃዋ የደቡብ አፍሪካ የምርጫ ኮሚሽን ቢሮ የሥራ ጉብኝት አድርጓል፡፡

 

የሁለቱ አገራት የኢኮሚ ግንኙነት

 • ከሁለቱ አጋራት መካከል በኢኮኖሚ ዘርፍ በርካታ የመግባቢያ ስምመኖቶች ተፈርመዋል፡፡ ከነሱም ዋና ዋናዎቹ አ.ኤ.አ. በኦገስት 1997 የግብርን ጥምረት ለመከላከል የተፈረመው ውል፣ በኦክቶብር 1998 የባህር ተራንስፖርት ትብብሩን ለማጠናከር የፈረመው ውል፣ በጁላይ 2000 የካይሮና የጁሃንስበርግን የንግድ ምክር ቤቶች ትብብር ለማጎልበት የተፈረመው ውል፣ እንዲሁም በዚያው አመት የግብጽ ንግድ መክር ቤት ፌሬሽንና የደቡብ አፍሪካ የሥራ ምክር ቤት ትብብርን ለማሻሻል የተፈረመው ውል፣ በ2009 በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ለጋራ ሥራ የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት እንዲሁም በ2016 የሁለቱ አገራት የአንቨስትመንት ባለስልጣናት በዘርፉ ትብብር ለማድረግ የፈረሙት ውል የሚሉት ናቸው፡፡

 

የንግድ ዘርፍ ትብብር

 • የሁለቱ አገራት ንግድ ልውውጥ መጠን በአለፉት አምስት አመታት ቀጣይነትያለው እድገት አሳይቷል፡፡ በ2013 132.3 ሚሊዮን ዶላር የነበረው መጠን በ2014 ወደ 151.2 ሚሊዮን ዶላር ከፍ ብሏል፡፡ ከዚያም በ2015 ወደ188.8 ሚሊዮን፣ በ2016 ወደ 266.3 ሚሊዮን፣ በ2017 ወደ314.7 ሚሊዮን ዶላር ከፍ ማለቱ ተመልክቷል፡፡
 • ግብጽ ወደደቡብ አፍሪካ ከምትልካቸው ምርቶች ዋና ዋናዎቹ፡ ቀጠን ያለ የሞተር ዘይት፣ ትኩስ ወይን፣ ከቦርስሊን የተሰሩ የሽንት ቤት መገልገያዎች፣ የመከሮናና ቲማቲም ሳልሳ ምርቶችና ደፍድፍ ነዳጅ ዘይት ሲሆኑ የነዳጅ ዘይቱ ዋጋ 35.4 ሚሊዮን ዶላር ይደርሳል፡፡ እንዲሁም የፖታሲየም ማዳበሪያ፣ መኪናዎችና የኮክ ድንጋይ ከሰል ምርቶች ወደደቡብ አፍሪካ ይላካሉ፡፡
 • ግብጽ ከደቡብ አፍሪካ የምታስመጣቸው ዋና ዋና እቃዎች ደግሞ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የእርሻ መኪና ተሳቢዎች፣ የአውቶብሳት ጎማዎች፣ ዝቅተኛ የጭነት መኪናዎች፣ የነሃስ ቱቦዎች፣ የጭማቂ ማዘጋጃ ማሽኖችና የድርና ማግ ማሽኖች ናቸው፡፡

 

የሚዲያ ዘርፍ ትብብር

 • በሚዲያ ዘርፍ ስልጠና አ.ኤ.አ. በ2017ና 2018 የሚዲያ ዘርፍ ግብጽ ባከሄደቻቸው ስልጠናዎች ከደቡብ አፍሪካ ታላላቅ ካዜጦችና የሚዲያ ተቋማት የተውጣጡ 16 ጋዜጠኞች ተሳትፈዋል፡፡ ስልጠናው የሚዲያ ሞያ፣ ጋዜጠይነት፣ የተሌቭዢን ፕሮግራም ቅንብርን አካቶ እንደነበር ታውቋል፡፡
 • በአሁኑ ወቅት ከግብጽ የመረጃ ኮርፖሬሽንና ከደቡብ አፍሪካው አቻው መካካል የመግባቢያ ስምምነት ለመፈረም ቅደመ ዘግጂት ላይ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ በ2003 ከደቡብ አፍሪካ ተሌቭዢን ጣቢና ከግብጽ ቴሌቨዢን ጣቢያ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል፡፡