የግብጽና የጂቡቲ ግንኙነት፡፡
ማክሰኞ ፣ ሚያዚያ 16 ቀን 2019
የግብጽና የጂቡቲ ግንኙነት፡፡

የሁለቱ አገራት ግንኙነት ታሪክ

 

   ግብጽና ጂቡቲ ልዩ የሆነ ታሪካዊና እስትራቲጃዊ ግንኙነት አላቸው፡፡ ግብጽ ጂቡቲ ነፃነቷን እ.ኤ.አ. በ1977 ከአገኘች በኋላ ቀደመው የድፕሎማት ግንኙት ከመሰረቱ አገሮች አንዷ ነበረች፡፡ሀገሪቱ የጂቡቲን የፖለቲካ አለመግባባት ከፍፃሜ ለማድረስ ከጂቡቲ መንግስትና ከተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል የተፈረመውን የፖለተካዊ ውይይት ማእቀፍ ስምምነት ፈጥና እንደደገፈችም ይታወቃል፡፡ በአንፃሩም ጂቡቲ በመላው አለም አቀፍ መድረኮች የግብጽን አቋም ስትደግፍ የቆየች ሲሆን በቅርቡም ከጁን 30 አቢዎት በኋላ የአፍሪካ ህብረት ተቀጥላ የሆነው የሰላምና ደህንነት ምክር ቤት በአፍሪካ ህብረት የግብጽን አባልነት በግዚያዊ መልኩ በአቆመበት ወቅት ጂቡቲ ውሳኔውን ተቃውማ ነበር፡፡

   የሁለቱን አገራት ግንኙነት በበለጠ ከሚያጠናክሯቸው ነገሮች መካከል ከግብጽ ብሄራዊ ደህንነት ምህዋሮች አንዱ እንደሆነ በሚታመነውና የስዊዝ ከናል ደቡባዊ መግቢያ በሆነው የባበል መንደብ ጠባብ መተላለፊያ በቀይ ባህር መግቢያ ላይ ያለችው የጂቡቲ እስትራቲጃዊ የመልከዓ ምድር አቀማመጥ ዋናኛው እንደሆነ ይነገራል፡፡ እንዲሁም ጂቡቲ በአላት ጠንካራ መሰረታዊ ግንባታና ዘመናዊ ወደቦቹዋ አማካይነት ለአፍሪካ ቀንድና ለመላው ምስራቅ አፍሪካ መግቢያ መሆኗም የሁለቱን አገሮች ግንኙነት እጅጉን አጠናክሮታል፡፡

 

የሁለቱ አገራት የፖለቲካ ግንኙነት፡፡

  የጅቡቲው መሪ ፕሬዝዳንት ኢስማኢል ዑመር ጌሌ እ.ኤ.አ. በ2016 በግብጽ ያደረጉት የሥራ ጉብኝት የሁለቱን አገራት ልዩ ግንኙነት አንጸባርቋል ሲሉ የፖለቲካ ታዛቢዎች ገልጸዋል፡፡ በዚያን ወቅት ፕሬዝዳንት ጌሌ ከግብጹ አቻቸው ፕሬዝዳንት አብደል ፈታሕ አልሲሲ ጋር ተገኛኝተው ከሁለቱም ወገን ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሚንስትሮች በተገኙበት የሀገራቱ ሁለገብ ትብብር የሚጠናከርበትን ሁኔታ መክረው ነበር፡፡ እንዲሁም በዚያን ወቅት ሁለቱ ወገኖች ግብጽና ጂቡቲን የሚመለከቱ ቀጠናዊና አለም አቀፍ ጉዳዮች፣ የአፍሪካ ቀንድና የየመን ጉዳዮች፣ የአፍሪካ ሳለምና ደህንነት፣ እየተባባሰ የመጣው የአህጉሯ ውዝግቦችና የአሸባሪዎች አደጋ የሚሉት ጉዳዮች  ተነስተው የተመከረባቸው መሆኑም ታውቋል፡፡ እንዲሁም እ.ኤ.አ በ18/11/2017 የጂቡቲው ውጭ ጉዳይ ሚንስተር ሚሰተር ኣሊ ማሕሙድ ዩሲፍ በግብጽ የሥራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ከግብጹ አቻቸው ሚስተር ሳሚሕ ሹክሪ ጋር ተገናኝተው የሁለቱን አገሮች የጋራ ግንኙነት፣የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች የሚሉትን ጉዳዮች ከመምከራቸውም በላይ የሁለቱን አገሮች የፖለቲካዊ ውይይት መካኒዝምን ማዋቀር የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመዋል፡፡

 

የሁለቱ አገራት የፖለቲካ ግንኙነት፡

 

  የግብጽና የጂቡቲ ግንኙነት እጅግ ጠንካራ ቢሆንም በዓመት ከ30 ሚሊዮን ዶላር የማይበልጠው የሁለቱ አገራት የንግድ ልውውጥ የአገራቱን ጠንካራ ግንኙነት አያንጸባርቅም፡፡ የጂቡቲው መሪ እ.ኤ.አ. በ2016 በግብጽ የሥራ ጉብኝት በአደረጉበት ወቅት በተለያዩ ዘርፎች የሁለቱን አገሮች ተብብር ለማጠናከር በርከታ ስምምነቶችና የመግባቢያ መስታወሻዎች ተፈራርመው ነበር፡፡ ሰምምነቱም፡ የሰጋ ከብትና ስጋ ማስመጣት ወይም ማስተላለፍ፣ የቴክኒክ ዘርፍ ትምህርት ልውውጥ፣ የዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን ተሳትፎ ልውውጥ፣ የንግድ የኢኮኖሚና የጤና ዘርፍ ትብብር የሚሉትን ዘርፎች አስመልክቶ ወደ33 ስምነቶች ደርሶ እንደነበር ታውቋል፡፡ የሁለቱ አገሮች የኢኮኖሚና ቴክኒክ ትብብር የጋራ ኮሚቴ ልዩ ልዩ ስብሰባዎችን አካሂዷል፡፡

  በጂቡቲ ያለው የግብጽ ኢምቨስትመንት በጀቡቲ የተለያዩ ኮንትራት ስራ በማከናወን ላይ ያለውን የእንጂነሮች አንደነትና በጂቡቲ የግብጽ ባንክ የቋቋመው የሹራ ኩባንያዎች ብቻ የተወሰነ መሆኑ ተነግሯል፡፡

 

የሁለቱ አገራት የባህል ትብብር፡

 

  የግብጽና የጂቡቲን የባህል ትብብር በማጠናከር ረገድ በርካታ የነጻ ትምህርት በመስጠት አል አዝሃር አልሸሪፍና የግብጽ ዩኒቨርስቲዎች ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ግብጽ በአፍሪካ ልማት የግብጽ አጋርነት ደርጅት አማካይነት በተለያዩ ዘርፎች ለጂቡቲ ወጣቶች የብቃት ዘርፍ ስልጠና ትሰጣለች፡፡ በአሁኑ ወቅት ከአስራ ሁለት በላይ የሚሆኑ የትምህርት ዘርፍ ልኡካን በጂቡቲ በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ የአልአዝሃር ዩነቨርስቲ በየዓመቱ ለጂቡቲ 15 የነፃ ትምህርት ይሰጣል፡፡ የጂቡቲው ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት እ.ኤ.አ. በ2016/2017 ሌላ 10 የሁለተኛ ደግሪ የነፃ ትምህርት ተወስኗል፡፡

 

 

 

 

የሁለቱ አገራት ወታደራዊ ትብብር፡

 

  ግብጽ በልዩ ልዩ ወታደራዊ ተቋሞቹዋና ኢንስቲትዮቶቹዋ አማካይነት በተለያዩ ዘርፎች ለጂቡቲ ወተዳራዊ ባለሞያዎች የቴክኒክ ድጋፍና የስልጠና እድል ተሰጣለች፡፡ በግብጽና ጂቡቲ ወታደራዊና ደህንነት ትብብር ማእቀፍ ስር የሽብርና ጸንፈንኝነት ተቃውሞ መካኒዝም ተዋቅሮ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ሁለቱ አገራት የቀይባህርን ከሽብርና ከዓለም አቀፍ የባህ ወሮ በላ አደጋ ለመከላከል የሚያስችል የጋራ ስራ ያከናውናሉ፡፡