ግብፅ እና ጋና
ግብፅ እና ጋና

 

ግብፅ እና ጋና

መግቢያ፡

ግብፅ እና ጋናን እ.ኤአ. በ1957 ጋና ከእንግሊዝ ነፃነቷን ካገኘችበት ከአለፈው ክፍለዘመን 50ዎቹ ጀምሮ ጠንካራ፣ ልዩና ታሪካዊ ግንኙነት ያስተሳስራቸዋል፡፡ ግብፅ ለጋና በተለይም ግብፅ ድጋፍ ታደርግለት ከነበረው የቀድሞው የጋና መሪ ፕሬዝዳንት ንክሮማ የስልጣን ዘመን ጀምሮ ለጋና ልዩ ትኩረት ትሰጣለች፡፡ እንደሚታወሰው የጋናን ነፃነት ትግል የመሩት የቀድሞው የጋና መሪ ፕሬዝዳንት ክዋሚ ንክሩማ ፈትህያ ንክሮማ የተባለችውን ግብፃዊት ነበር ያገቡት፡፡ ግብፅ ከጋና ጋር የድፕሎማት ግንኙነት ከመሰረቱ ቀደምት አገሮች አንዷ ነበረች፡፡ ይሀውም ፕሬዝዳንት ንክሮማ የቀድሞው የግብፅ መሪ ፕሬዝዳንት ጀማል አብደል ናስር የቅርብ ጓደኛ ስለነበሩ ነው፡፡

    አንዳንድ ሰዎች የግብፅ እና የጋና ግንኙነት በአፍሪካ አህጉር የነፃነት ንቅናቄ በተቀጣጠለበት በአለፈው ክፍል ዘመን 50ዎቹ አካባቢ እንደጀመረ ይገምታሉ፡፡ እውነቱ ግን ከዚያ በፊት ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ ሲሆን የሁለቱ አገሮች ግንኙነት ከዚያ በፊት በመካከለኛው ክፍለ ዘመናት አንደሌሎቹ የአፍሪካ ንጉሳዊ ግዛቶች የጋና ንጉሳዊ ግዛት የእስልምናን እምነት ተቅብሎ ከሙስሊም አገሮች ጋር ግንኙነት ማድረግ በጀመሩበት ወቅት ከነዚያ ሙስሊም አገራት ግብፅ ቀደምትነትን በያዘችበት ወቅት ነበር የጀመረው፡፡ የጋና ህዝብ ሀገሪቱ ነፃነቷን ካገኘች በኋላ የሀገሪቱ የመጀመሪያ መሪ ኩዋሚ ንክሮማ ጋናውያን እንደሚጠሯት የአባይ ሙሸራ (ፈትሕያን) ለማግባት ከወሰኑበት ጊዜ ጀምሮ ከግብፅ ጋር ጥብቅ ትስስር እንዳደረገ ይታመናል፡፡ ጋናውያን ወ/ሮ ፈትሕያን እጅግ ያደንቁ እንደነበርና ንክሮማ ወደ ግብፅ ሄዶ በአባይ ሙሽራ ተመለስ ይሉ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ወ/ሮ ፍትሕያና ባለቤታቸው ንክሮማ ከዚህች ዓለም በሞት ከተለዩ ዓመታት ቢቆጠሩም ጋናውያን ዛሬም ያስታውሷታል ስለቁንጅናዋም ያወራሉ፡፡ እሷ ጋናን ከልብ እንደወደደቻት ሁሉ የጋናም ህዝብ ያንኑ ያህል ፍቅር ችረዋታል፡፡ ወ/ሮ ፈትሕያ በሀገሪቱ ድሆችን ትረዳና የሙታን ልጆችን ትንከባከብ ስለነበረ  በጋናውያን ልብ ከፍተኛ ፍቅርን አሳድረው እንደነበር ይነገራል፡፡ ወ/ሮ ፈትሕያ ግብፃዊነቷንም አልዘነጋችም ነበር፡፡ ከ1967ቱ ሽንፈት በኋላ ለሀገሪቱ ጦር ወጭ እገዛ የነበራትን ጌጣጌጥ በሙሉ ለካይሮ ባንክ አስርከባ እደነበር ይታወቃል፡፡

    የጋናው መሪ ኩዋሚ ንክሮማ ታለቅ ልጅ ጀማል ንኩሮማ እንደሚገልጹት እናታቸው ፈትሕያ ፕሬዝዳንት ንክሮማን ከገለበጠው ከ1966ቱ  ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት በኋላ ከፍተኛ ወዝግብ ቢደርስባቸውም አንኳ ለግብፅ ሀገራቸው ያለባቸውን ግዴታ ከመወጣት ወደኋላ ብለው አያውቁም፡፡ ጀማል ንክሮማ ትዝታቸውን እንዲህ በማለት ይገልጻሉ፡ በጋና መፈንቅለ መንግስቱ የተከሰተ ለት ማለዳ እናቴ ለጀማል አብደል ናስር ስልክ ደውላ መፍትሄ እንዲፈሉጉላት ጠየቀች እሳቸውም አረጋጓት በዚያን ዕለት ልዩ አውሮፕላን ልከው ወደ ካይሮ መጣን መኣዲ ያለው ቤታችን እስከሚዘጋጅም ለሦስት ወር ያህል በጧህራ ቤተመንግስት ተቀመጥን፡፡ በግብፁ ፕሬዝዳንት ስም የተጠሩት የንክሮማ ልጅ በመቀጠልም እንዲህ ይላሉ፡ ፕሬዝዳንት ናስር የአባቴ የቅርብ ጓደኛ ነበሩ ሴት አያቴ በመጀመሪያ እናቴ አባቴን እንድታገባ ፈቃደኛ አልነበረችም ነገር ግን ፕሬዝዳንት ናስር ምን ያስፈራሻል ልጅሽ ታላቅ አፍሪካዊ መሪ ነው የምታገባው፡፡ በቅርቡም ጋና ውስጥ የግብፅ ኢምባሲ እከፍታለሁ፡፡ እንዲሁም የቀጥታ በረራ መስመርም እንከፍታለን፡፡ በፈለግሺበት ጊዜ ልጅሽን መጎብኘት ትችያለሽ በማለት አሳመኗት ትዳሩም ተመሰረተ፡፡ ሰለመላ ቤተሰቡም እንዲህ በማለት ጀማል ንክሮማ ያብራራሉ፡ ከዚያም በኋላ እናቴ ወደጋና ተሳፈረች፡፡ እዚያ ስንኖርም አያቴ እየተመላለሰች ትጠይቀን ነበር፡፡ በ1972 አባቴ ከሞተ በኋላም እንኳ እናቴ ከአባታችን አገር እንድንቋረጥ አልፈቀደችም፡፡ ወደ ጋና ተመልስን ከዚያም እኔ ለትምህርት ወደ ለንደን ሄድኩ ወንድሞቼ አዚያው ኑሯቸውን መምራት ቀጠሉ እኔ ግን ትምህርቴን ጨርሼ ወደ ግብፅ ተመልሼ እዚህ ኑሮየን ቀጠልኩ፡፡በተለያዩ መስኮች ያሉት የግብፅ እና የጋና ትብብር ገጽታዎች በርካታዎች ናቸው፡፡ ከእነሱም በቀደምትነት የሚጠቀሰው ጋና የሀገሪቱን የቱሪዝም ዘርፍ ለማሳደግ የምታደርገውን ጥረት ግብፅ የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተቀጥላ የሆነው ለአፍሪካ ልማት የግብፅ አጋርነት ኤጀንሲ በሚያዘጋጃቸው የስልጠና ፕሮግራሞች ጋናውያን የዘርፉ ባለሙያወችን በማሳተፍ የምታደርገው ድጋፍ ነው፡፡ በጋና የመሰረተ ልማት ግንባታ ሂደትም የግብፅ ተቋራጭ ኩባንያዎች እንዲሳተፉ መንግስት ድጋፍ ያደርጋል፡፡

  የግብፅ እና የጋናን ግንኙነት ለየት የሚያደርገው በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በባህል ዘርፎች ግብፅ ከምታደርገው ድጋፍ አንፃር በጥልቅ ታሪካዊነቱና በመከባበር የተመሰረተ መሆኑ ነው፡፡ ግብፅ ለጋና ልዩ ልዩ እርዳታ የምታበረክት ከመሆኗም ባሻገር በጤና፣ በደህንነት፣ በማስታወቂያና ቱሪዝም ዘርፎች የጋና ካድሬዎችን ታሰልጥናለች፡፡ የዚህ ዓይነቱ የግብፅ ድጋፍ የጋና ባለሙያወች የቴክኒክ ብቃት እንዲበለፅግ ታላቅ አስተዋጽኦ ያደረገ ሲሆን ጠቃሚነቱ  ማሀበረሰቡ ለጋና አጠቃላይ ልማት በሚያደርገው ጥረት ጎልቶ ይታያል፡፡

የሁለቱ አገሮች የኢኮኖሚና የልማት ትብብር

  • እ.ኤአ. በ5/12/2017 የግብፁ የመገናኛና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚነስቴር ኢንጂነር ያሲር ኢልቃዲና የጋናው አቻቸው ዮርሶላ ኦዋሶ አፎኮል በመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ የሁለቱን አገራት ትብብር ለማጠናክር የሚስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ውሉ የምንግስትና የግል ድርጅቶችን ፋይዳ ለማስፋት የሁለቱን አገሮች የስልጠና እድል ማጎልበትና ማሻሻል፣ የፖሊሲ ነደፋን ጠለቅ ያለ ማድረግ፣ ምርምርና ፈጠራ ማሻሻልና የሥራ አመራርን ማበልፀግ የሚሉትንም ዘርፎች አካቷል፡፡ ይሀው በጋና የቴክኖሎጂ ክልል መመስረት፣ በኤሌክትሮኒክስ ፕሮግራም የግብፅ ተሞክሮ ውጤት ወደ ጋና ለማሸጋገር፣ ግዙፍ የመረጃ ማዕከል ማዋቀር ለባህል ቅርሶችና ለተፈጥሮ ሀብት ማረጋገጫ መስጠት በሚሉት ዘርፎች የሁለቱ ሀገራት ሚኒስቴሮች በጋራ እንዲሰሩ የሚያስችለው ውል ለሁለት ዓመታት ይዘልቃል፡፡

 

  • የግብፅ እና የጋና ግንኙነት ሁለቱም አገራት የየሀገራቸውን ልማት ሂደት ለማፋጠን አንዱ ከሌላው አቅም፣ ልምድና ክህሎት ለመጠቀም ከሚያደርጉት ሙከራ አንፃር ግንኙነታቸው በተለይም ደግሞ በኢኮኖሚና በልማት ዘርፎች ያለው ትብብራቸው ከፍተኛ እድገት እያሳየ መጥቷል፡፡ በጋና የግብፅ ኢኮኖሚ ቦታ መያዝ የጀመረው ግብጻዊው ባለሀብት ሚስተር ሚድሐት ኸሊል በአሁኑ ወቅት በምእራብ አፍሪካ በዘርፉ ተወዳዳሪ የሌለውንና በክልሉ መልካም ዝና ያተረፈውን የአልሙኒየም ኩባንያ ጋና ውስጥ በከፈቱበት ወቀት ነበር፡፡ እንዲሁም ነስር አስመጭና ላኪ ኩባንያ የጋናን ካካውና እንጨት ምርት ወደ ግብፅ የማሰገባት ሥራውን የጀመረው ባለፈው ክፍለ ዘመን አምሳዎቹ አካባቢ ነበር፡፡ ኤሌክትሮ ሜትር የተሰኘ የግብፅ ኩባንያ ጋና ውስጥ የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ኢንዱስትሪ ከፍቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ አልካንና አጂ ፕሮ የተሰኙት የቴሌኮም ድርጅቶች ባለቤትነታቸው ግብፃዊ ባለሀብቶች መሆናቸው ይታወቃል፡፡ የአረብ ኮንትራክተር ኩባንያ በጋና የቮልታ ባህር የሚሰሩ ሶስት ታላላቅ መርከቦችን ሰርቶ ለአገልግሎት አብቅቷል፡፡ አንዲሁም የመሀንዲሶች አንድነት ኩባንያ በጋና ዋና ከተማ አክራ በተለያዩ የግንባታ ሥራዎች ተሰማርቶ ይንቀሳቀሳል፡፡ እነዚህ ሁሉ እንቅስቃሴዎች የግብፅ አየር መንገድ በረራ እንዲጨምር ያደረጉ ሲሆን በሳምንት አራት ጊዜ ቀጥታ በረራ እንዲወስን አድርገዋል፡፡

 

  • የግብፅ እና የጋና የኢንቨስትመንት መድረክ በ8/12/2010 ካይሮ ውስጥ የተካሄደ ሲሆን የጋናው ምክትል ፕሬዝዳንት ሜስተር ጆን ማሃማ ነበሩ መርቀው የከፈቱት፡፡ በዚያም ወቅት በሁለቱም አገሮች ያሉ የኢንቨስትመንት እድሎች ማብራርያ ተሰጥቶባቸው ነበር፡፡

 

  • ግብፅ እና ጋና በቱሪዝም፣ በባህር ትራንስፖርት፣ በእርሻ፣ በጤናና በሌሎችም ዘርፎች በርካታ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል፡፡

 

  • ጋና በቅርቡ የነዳጅ ዘይትና የተፈጥሮ ጋዝ ማምረት የጀመረች ሲሆን በዚህ ዘርፍ የግብፅን ተሞክሮ ውጤት ተግባራዊ ለማድረግ ፍላጎት እንዳላት ገልፃለች፡፡ እንዲሁም በጥጥና በጨርቃጨርቅ ዘርፍ ከግብፅ ልምድ ለመቅሰም ጥረት እንደምታደርግ ተመልክቷል፡፡ ይህም ጋና የምእራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማሀበረሰብ ኢክዋስ አባል እንደመሆኗ በርካታ የግብፅ የጨርቃጨርቅ አምራች ኩባንያዎች በምእራብ አፍሪካ ለመንቀሳቀስ ካላቸው ፍላጎት ጋር የተጣጣመ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

 

  • የግብፅ እና የጋና ግንኙነት በተለይም በኢኮኖሚና ልማት ዘርፍ ከፍተኛ እድገት እያሳየ መጥቷል፡፡ እ.ኤአ. በ2012 በተደረገ ግምገማ የግብፅ እና የጋና የንግድ ልውውጥ ወደ 82 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የደረሰ ሲሆን ግብፅ ወደ ጋና የላከችው ምርት መጠን 70 ሚሊዮን ዶላር ግብፅ ከጋና ያስመጣችው ምርት መጠን 12 ሚሊዮን ዶላር ነበር፡፡

 

  • ከግብፅ ወደ ጋና የሚላኩት ዋና ዋና ምርቶች የግንባታ ግብኣቶች፣ የግድግዳ ቀለሞች፣ ሲሚንቶ፣ የአርማታ ማቀፊያ ብረቶች፣ የተዘጋጁ ምግብና መጠጦችና አውቶብሶች ሲሆኑ ግብፅ ከጋና የምታስገባቸው ምርቶች ደግሞ ካካውና ለኢንዱስትሪ አግልግሎት የሚውሉ የእንጨት ምርቶች ናቸው፡፡

 

 

በግብጽ ና በጋና መካከል የተደረጉ የጉብኝት ልውውጦችና የእንቅስቃሴ ተሳትፎዎች፡፡

 

  • የግብፁ መሪ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አል ሲሲ እ.ኤ.አ. ሴፕተምበር 18 2017 ኒው ዮርክ ዩ ኤስ አሜሪካ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ጉባኤ ጎንዮሽ ከጋናው አቻቸው ፕሬዝዳንት ናና አኮፎ አዶ ጋር ከተወያዩ በኋላ በሰጡት መግለጫ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት ማጠናከርና የሁለቱን አገሮች የንግድ ልውውጥ ወደ ፖለቲካዊው ግንኙት ደረጃ ማሳደጉ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ በጋና ያለው የግብፅ ኢንቨስትመንት ዘርፈ ብዙ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ የጋናው መሪ በበኩላቸው ሀገራቸው ከግብፅ ጋር በአላት ታሪካዊ ግንኙነት የምትኮራ መሆኗን አመልክተው በሁሉም ዘርፍ ያለውን የሁለቱን አገሮች ትብብር ለማጠናከር ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ የጋናው መሪ ግብፅ በአቅም ግንባታ ዘርፍ ለጋናውያን የምታደርገውን ቀጣይ ድጋፍም ከልብ እንዳወደሱ አስታውቀዋል፡፡ በመጨረሻም በደህንነትና በሽብር ተቃውሞ መስክ ከግብፅ ተሞክሮ ለመጠቀም ሀገራቸው ያለትን ጽኑ ፍላጎት አውስተዋል፡፡