ግብፅ
 ግብፅ

ግብፅ ወይም ምጽር፣ ምሥር (አረብኛ مصر ) በሰሜን ምስራቅ ኣፍሪካ የምትገኝ አገር ናት። 104.2 ሚሊዮን ከሚሆነው ህዝቧ አብዛኛው ከናይል ወንዝ ዳርቻ በአንድ ኪሎሜትር ክልል ውስጥ ይገኛል። የግብፅ አብዛኛው መሬት በሰሃራ በረሃ ክልል ውስጥ ይገኛል። ዋና ከተማዋ ካይሮ ስትሆን ከአፍሪካም ትልቋ ከተማ ናት። ሌላ ትኩረት የሚሰጣት ከተማ አሌክሳንድሪያ (እስክንድርያ) ናት። አሌክሳንድሪያ የአገሪቱ ዋና ወደብ ስትሆን በህዝብ ብዛት ከአገሪቱ ሁለተኛ ናት።

   ግብፅ በሰሜን ከሜዴቴራኒያን ባሕር በምሥራቅ ከቀይ ባሕር፤ በደቡብ ከኖብያ፤ በምዕራብ ከምድረ በዳው አገር ይዋሰናል። ነጭ አባይ በግብፅ መካከል ያደርግና ከደቡብ ወደ ምሥራቅ ይሄዳል። የአባይ ወንዝ የሚሞላው በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ነው። በግብፅ የሚዘንበው አንድ አንድ ጊዜ ብቻ ስለ ሆነ ግብፅ በአባይ ለምቶ ይኖራል።

ታሪክ

ጥንታውያን የግብጽ ባለሥልጣኖች

   በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ከማየ አይኅ ቀጥሎ መጀመሪያ የአፍሪካ ሕዝብ የኖኅ ልጅ የካም ዘሮች ናቸው፤ ይህ አገር ሰናዖር ለሚሉት ቅርብ ስለ ነበር የባብል ግንብ ከተሠራ በኋላ ከዚህ ተነስተው ወደ ግብፅ ወረዱ።

   የግብጽ ቀድሞ ዘመን መንግሥት ዋና ጥንታዊ ነው፤ የመሠረተውም ፈርዖን ሜኒስ የተባለው ነው። ጸሓፊው ጊዮርጊስ ስንቄሎስ (፰፻ ዓ.ም. አካባቢ የጻፈው) ይህ ፈርዖን ሜኒስ በዕውነት የካም ልጅ ምጽራይም እንደ ነበረ ገመተ።

   ዳሩ ግን አባ አውሳብዮስ በጻፉት ዜና መዋዕል ዘንድ (፫፻፲፯ ዓ.ም. ተጽፎ)፣ የድሮ ግብጻዊው ባለታሪክ ማኔጦን (፫ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ.) ስለ ኋለኞቹ ግብጻውያን ሲጽፍ፣ ይኮሩበት የነበረው የታላቁ ጥንት ዘመን ከማየ አይህ አስቀድሞ እንዳለፈ፣ በኋላም በዚያው አገር ዳግመኛ ከሠፈረበት ከካም ልጅ ምጽራይም በውኑ እንደ ተወለዱ ጽፎ ነበር። ተመሳሳይ ታሪክ በእስላም ጸሐፊዎች በግብጻዊው እብን አብድ ኤል-ሀከም እና በፋርሳውያን አል-ታባሪና ሙሐመድ ቈንዳሚር መጻሕፍት ሲገኝ፣ ፒራሚዶች፣ እስፊንክስ ወዘተ. ሁሉ የተሠሩ ከጥፋት ውኃ በፊት በኖሩት ክፉ ዘሮች ሆኖ፣ ከዚያ በኋላ ግን አገሩ ለካም ተወላጅ ለምጽራይም ('ማሣር' ወይም 'መሥር') ተሠጠ ብለው ጻፉ።

   በግሪኩ ጸሐፊ ሄሮዶቶስ ዘንድ፣ የግብፅ ቀድሞ ዘመን የመጀመሪያው ፈርዖን ሜኒስ ነጭ አባይን ከመነሻው ወደ ጎን መለሰና ውሃው ይፈስበት በነበረው ላይ ሜምፊስ የተባለውን ከተማ ቆረቆረ። ታላቅ ንጉሥም ስለ ነበረ ከሞተ በኋላ ሕዝቡ እንደ አምላክ አድርገው አመለኩት። በዘመናዊ አስተሳስብ፣ ይህ ላይኛ ግብጽና ታችኛ ግብጽ ያዋሐደው መጀመርያው ፈርዖን መታወቂያ ለሥነ ቅርስ ከሚታወቀው ፈርዖን «ናርመር» ከተባለው ጋር አንድ ነው።

ናርመር (ሜኒስ) አገሩን ካዋሐደ አስቀድሞ ሌሎችም ነገሥታት (ለምሳሌ ንጉሥ ጊንጥ) በአገሩ ክፍሎች ብቻ ላይ እንደ ነገሡ ከተገኙት ቅርሶች (የመንደሮቹ መኳያ ሰሌዳ ወይም የጊንጥ ዱላ እንደሚያሳይ) ይታወቃል።

    የሃይሮግሊፍ ቅርሶችና መዝገቦች ለማንበብ ችሎታው አሁን ስላለ፣ ሜኒስ ከነገሠ በኋላ የግብፅ ታሪክ በጥቂት መጠን ተገልጾአል። መጀመርያው ሥርወ መንግሥታት (፩ኛው እስከ ፮ኛው ድረስ) የቀድሞ ዘመን መንግሥት ይባላሉ። በ፩ኛው ሥርወ መንግሥት ሰባአዊ መስዋዕት በሰፊ ይደረግ ነበርና ከፈርዖኖቹ ጋራ ብዙ ሎሌዎች አብረው ይቀበሩ ነበር። የሔሩ ወገን በሴት ወገን ላይ ይበረታ ነበር። በ፪ኛው ሥርወ መንግሥት የፈርዖኖች መቃብር ከተማ ከላይኛ ግብጽ ወደ ታችኛ ግብጽ (ስሜኑ) ተዛወረ። በኋለኛ 2ኛው ሥርወ መንግሥት ዘመን የሴት ወገን ወኪል ፈርዖን ፐሪብሰን ተነሣና ያንጊዜ ትግሎች እንደ በዙ ይመስላል። በ፫ኛው ሥርወ መንግሥት መጀመርያ የሔሩ ወገን ለሥልጣን ተመልሶ፣ ነጨሪኸትየተባለው ፈርዖን የመጀመርያውን ሀረም (ፒራሚድ) አሠራ። ከርሱም በኋላ የተነሡት ታላላቅ ፈርዖኖች በጊዛ ሜዳ ላይ ፒራሚዶቻቸውን እንዲሁም የጊዛ ታላቅ እስፊንክስን ሠሩ። በ፬ኛውም ሥርወ መንግሥት የፈርዖኖች ዝሙት የገዛ እኅቶቻቸውን እስከሚያግቡ ድረስ ደረሰ። በ፭ኛው ሥርወ መንግሥት መጨረሻ ፈርዖኖች በሀረሞቻቸው ውስጥ የሀረም ጽሕፈቶች ያስቀረጹ ጀመር፤ እነኚህ ጽሕፈቶች የሔሩ ተከታዮች ወገን (ወይም «ደቂቃ ሔሩ») በሴት ተከታዮች ወገን ላይ የፈጸሙትን ጨካኝ የጭራቅነት ሥነ ስርዓት ይመሰክራሉ። ይህም አስጨናቂ ሁኔታ በ፮ኛው ሥርወ መንግሥት እየተቀጠለ ፈርዖኖቹ ዓለማቸውን ሁሉ ከነጎረቤቶቻቸውም ጋር በጽናት ይገዙ ነበር።

   ፮ኛው ሥርወ መንግሥት ከነገሠ በኋላ የግብፅ ታሪክ እጅግ ግልጽ ሆኖ አይታይም። በታሪክ ጸሐፍት እንደ ማኔጦን ዝርዝሮች በኩል፣ ለ፯ኛው-፰ኛው ሥርወ መንግሥታት በርካታ ስሞች ቢመዘገቡም፣ ከጥቂቶቹ ብቻ በስተቀር አንዳችም ሥነ ቅርሳዊ ማስረጃ ከቶ ስላልተገኘላቸው፣ ስሞች ብቻ ቀርተው በእውነት እንደ ኖሩ ወይም ዝም ብለው በማስመስል እንደ ተፈጠሩ አይታወቀም። ከቀድሞውም ዘመን በኋላ በእርግጥኛነት የነገሡት መጀመርያ ፈርዖኖች የግብጽ መካከለኛውን ዘመን መንግሥት የመሠረቱት በስማቸውም ውስጥ «ታ-ዊ» (ሁለቱ አገራት ወይም በዕብራይስጥ ምስራይም) የተባሉት ናቸው።

 

የግሪክ ጸሐፍት አፈ ታሪክ[ለማስተካከል

    በ6ኛው ሥርወ መንግሥት መጨረሻ ኒቶክሪስ የተባለች ሴት የአገሩ ንግሥት እንደ ሆነች የሄሮዶቶስና የማኔጦን ታሪኮች ይነግራሉ። ሄሮዶቶስ እንደሚለው፣ ወንድሙዋን ግብፆች ስለ ገደሉባት እሷም ልትበቀልለት አሰበች። ለዚሁ ጉዳይ ከመሬት ውስጥ አንድ ታላቅ አዳራሽ አሠራች። ከዚያም ታላቅ ግብር አዘጋጅታ የወንድሙዋን ገዳዮች ወደዚሁ ግብር ጠራቻቸው። የተጠሩትም በግብፅ ግዛት የታወቁ ክቡራን ነበሩ። እንዲሁ ሆኖ ሳለ በድንገት ከውጪ በራሳቸው ላይ ውካታና ፍጅት ጩኸትም ተነሳ። የጥፋት ውሃ አዳራሹን ሰብሮ ገባ። ንግሥት ኒቶክሪስ አስቀድማ የወንዙን ውሃ በሚስጥር ወደ አዳራሹ እንዲገባ አድርጋ ነበርና ውሃው በዚያ ታላቅ ግብር ላይ እንዲለቀቅ አደረገች። በዚያም የገቡ ሁሉ ሰጥመው ቀሩ። ይህ የኒቶክሪስ ታሪክ በሄሮዶቶስም ሆነ በማኔጦን ቢገኝም፣ በዘመናዊ ሥነ ቅርስ አስተያየት ለዘመንዋ ምንም ማስረጃ ስላልተገኘ አሁን እንደ አፈ ታሪካዊ ንግሥት ብቻ ትቆጠራለች።

   በግሪኮች የታሪክ ጸሐፍት ዘንድ ሌላ ስመ ጥሩ ፈርዖን ሲሶስትሪስ ነበር። ይህ ንጉሥ ዓለምን ለማሸነፍ አስቦ ከግብፅ ሲነሣ የሚሊዮን እኩሌታ የሚሆኑ እግረኛ ወታደሮች፣ ፳፬ ሺህ ፈረሰኞች፤ ፳፯ ሺህ የተሰናዱ ሠረገሎች እንደ ነበሩት ይተረኩ ነበር። ዝና ፈላጊነቱ በክብር ተፈጸመለትና ትልቅ ድል አገኘ። በየሄደበት ስፍራ ሁሉ ከእብነ በረድ የተሠራ ሐውልት አቆመ። የሚመጣው ትውልድ እንዳይረሳው ባቆመው ሐውልት ላይ ጽሕፈት እንዲቀረጽበት አደረገ። በብዝዎቹ ሐውልት ላይ እንዲህ የሚል ቃል ተጽፎአል።

«ንጉሠ ነገሥት ሲሶስትሪስ በጦር ሠራዊቱ ኅይሉ ይህን አገር አሸንፎዋል»

ነገር ግን ዘመናዊ የታሪክ ጸሓፊዎች እንደዚህ አላደረገም ብለው ይጠራጠራሉ። በማኔጦን ነገሥታት ዝርዝር «ሴሶስትሪስ» የሚባል ፈርዖን በ12ኛው ሥርወ መንግሥት በፈርዖን 3 ሰኑስረት (ሰንዎስረት) ፋንታ ይታያል። ስለዚህ የሴሶስትሪስ አፈ ታሪክ ከሰንዎስረት ትዝታ እንደ ተወረደ ይታመናል።

ስነ ፈለካዊ አቀማመጥ

የግብጽ ስነ ፈለካዊ አቀማጥ በሰሜን ምስራቅ መስመር ከኬክሮስ  22 - 23 እና በግሪኒች መስመር ምስራቀዊ ክፍል ከኬንትሮስ  24 - 37  መስመር መካከል እንደሆነ ይታወቃል፡፡

የመልክዓ ምደር አዋሳኝ ክልሎች

ግብጽ አረብ ሪፐብሊክ በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ የምትገኝ አገር ስትሆን በሰሜን 995 ኪ.ሜ.ርዝመት ያለው የሜድትራንያን ባሕር ዳርቻ፣ በምስራቅ 1941 ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው የቀይ ባሕር ዳርቻ፣ በሰሜን ምስራቅ -በ265 ኪ.ሜ. ርዝመት-ፍልስጤምና እስራኢል፣ በምእራብ -በ 1115 ኪ.ሜ.- ሊብያ፣ በደቡብ - በ1280 ኪ.ሜ ርዝመት- ሱዳን ሪፐብሊክ ያዋሰኗታል፡፡

የቆዳ ስፋት መጠን፡ የግብጽ አረ ብሊክ የቆዳ ስፋት 1.002.000 ኪሎሜትር ሲሆን ህዝብ የሚኖርበት ክልል 78990 ሜትር  ብቻ ነው፡፡ ከአጠቃላይ የሀገሪቱ ቆዳ ስፋት 7.8% ይሆናል፡፡

የአየር ጠባይ

 

   በግብጽ የአየር ሁኔታ በርካታ ነገሮች ተጽእኖ የሚያሳድሩ ሲሆን የጅኦግራፊ አቀማመጥ፣ የወለል ገጽታና በአየር ግፊት፣ ወንዞችና የውሃ ወለል አጠቃላይ ሁኔታ የሚሉት በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳሉ፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ታዲያ ግብጽን ወደ ልዩ ልዩ የአየር ጠባይ ክልሎች ከፋፍለዋታል፡፡ ከዚህም አኳያ ግብጽ በደረቃማው የሐሩር ክልል የምትገኝ ሲሆን ጥቂት የሰሜን ጠረፍ አካባቢዋ በበጋ ወራት ደረቅ ሞቃታማ፣ በክረምት ደግሞ ቀላል ዝናብ በተለይም ባሕር ዳርቻው ክፍል በሚያገኘው የሜድትራንያን  ክልል እየተባለ በሚታወቀው የመካከለኛ ሙቀት ክልል ይካተታል፡፡  

   በአጠቃላይ የግብጽ የአየር ጠባይ ወደሁለት ወራቶ ሊከፈል ይችላል፡፡ እነሱም አንደኛው ከሜይ ወር እስከ ኦክቶበር የሚዘልቀው የበጋ ወራት ሲሆን ደረቅ ሙቀታማ ገጽታ አለው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ከኖቨምበር ወር አስከ አፕሪል ወር የሚዘልቀው የክረምት ወራት ሲሆን ከቀላል ዝናብ ጋር የለዘብተኛ ሙቀት ገጽታ የሚታይበት ወራት ነው፡፡

የግብጽ የአየር ሙቀት መጠን

   በጃንዋሪ ወር ዝቅተኛው የሙቀት ደረጃ ከ9 እስከ 11 ሴንቲ ድግሪ ሲሆን ከፍተኛው ደግሞ ከ20 እስከ 24 ሴንቲ ድግሪ ይሆናል፡፡ በጁላይና ኦገስት ወራቶች ደግሞ ዝቅተኛው የአየር ሙቀት መጠን ከ21 እስከ 25 ሴንቲ ድግሪ ሲሆን ከፍተኛው ደግሞ ከ37 እስከ 42 ሴንቲ ድግሪ ይደርሳል፡፡

ተራራዎች

የግብጽ አረብሪፐብሊክ ተራራዎች ወደአራት ዋናዋና ክፍሎች ይከፈላሉ፡

  • የደልታና የአባይ ተፋሰስ ተራራዎች፡

33000 አካባቢ ካሬ ሜትር ስፋት ያለው የደልታና የአባይ ተፋሰስ ክልል ከሀገሪቱ አጠቃላይ መልከዓ ምድር ስፋት 4% የሚሆነውን ክፍል ይሸፍናል፡፡ የአባይ ተፋሰስን ስንመለከት ከስተደቡብ ከሰሜናዊ ሐልፋ ሸለቆ ይጀምርና አስከ ሜድትራንያን ባህር ዳርቻ ይደርሳል፡፡ ከሐልፋ እስከ ደቡባዊ ካይሮ ያለው ከፍል ላይኛው ግብጽ በመባል ይታወቃል፡፡ ከሰሜናዊ ካይሮ አስከ ሜድትራንያን ባህር ዳርቻ ደረስ ያለው ክፍል ደግሞ ታችኛው ግብጽ ዌም ደልታ -ደለል- በመባል ይታወቃል፡፡የአባይ ርዝመት ግብጽ ምድር ከሀገሪቱ ደቡባዊ ድንበር ጀምሮ እስከ መዳረሻው የሜድትራንያን ባህር ዳርቻ ድረስ 1532 ኪሎ ሜትር አካባቢ ነው፡፡ የአባይ ወንዝ ሰሜናዊ ካይሮ ላይ የድምያጥ ገባርና የረሺድ ገባር በመባል ወደሚታወቁ ሁለት ዋናዋና ቅርንጫፎች ተከፍሎ ሁለቱ ቅርንጫፎች በግብጽ እጅግ ለም የሚባለውን የደልታን ምድር አቅፈው ይዘውታል፡፡

  • የምዕራብ ሰሃራ ተራራዎች

የምዕራብ ሰሃራ መልክዓ ምድር ስፋት 680 ካሬ ኪሎ ሜትር አካባቢ ሲሆን ከአጠቃላይ የግብጽ መልከዓ ምድር ሰፋት 68% የሚሆነውን ክፍል ይሸፍናል፡፡ የምዕራብ ሰሃራ ከስተምስራቅ ከአባይ ተፋሰስ ጀምሮ በምዕራብ እስከ ሊብያ ድንበር ይደርሳል፡፡ እንዲሁም ከስተሰሜን ከሜድትራንያን ባህር ዳርቻ ጀምሮ እስከ ደቡባዊ ድንበር ይዘልቃል፡፡

ሰሜናዊ ክፍል

የክልሉ ሰሜናዊ ክፍል የባህር ዳርቻ ሳህል፣ የሰሜን ተራራና ታላቁ ሸለቆ ክልልን የሚያካትት ሲሆን በዚህኛው ክልል የሲዋ የበረሀ ገነት፣ የቀጣራ ሸለቆ፣ የነጥሩን ተፋሰስና የባህርያ ባህረ ገነት ይካተታሉ፡፡

ደቡባዊ ክፍል

የምዕራብ ሰሃራ ደቡባዊ ክፍል የፈራፍራ፣ ኻሪጃና ዳኺላ በረሀ ገነቶችን እንዲሁም በደቡባዊ ጠረፍ የሚገኘውን የኡወይናትን በረሀ ገነት ያካትታል፡፡

  • የምስራቅ ሰሃራ

የምስራቅ ሳሃራ የመልከዓ ምድር ስፋት 225000 ካሬ ኪሎ ሜትር አካባቢ ሲሆን ከአጠቃላዩ የግብጽ መልከአ ምድር ስፋት 28% የሚሆነውን ክፍል የሚሸፍን ሲሆን የሲናው ደሴት መሰልም በዚሁ ክልል ይካተታል፡፡ክልሉን በስተምዕራብ የአባይ ተፋሰስ፣ በስተምስራቅ ቀይ ባህር፣ የስዊዝ ባህር ወሽመጥና የስዊዝ ካናል፣ በስተሰሜን በሜድትራንያን የሚገኘው የመንዘላ ሓይቅና በስተደቡብ ደግሞ የሱዳን ድንበር ያካልሉታል፡፡ ምስራቅ ሳሃራን ከሚለዩት ገጽታዎች በቀይባህር ዳርቻ የሚገኙት ከባህር ወለል በላይ እስከ3000 ጫማ ከፍታ ያላቸው ተራራዎች ሲሆኑ ለግብጽ እንደ ወርቅ፣ የድንጋይ ከሰልና የነዳጅ ዘይት ያሉ የተለያዩ ማዕድናት የተፈጥሮ መጋዘን እንደሆኑ ይነገራል፡፡

  • የሲናይ ደሴት መሳይ

የሲናይ ደሴት መሳይ ክልል መልከዓምድር  ስፋት 61.000 ካሬ ኪሎ ሜትር አካባቢ ሲሆን ከአጠቃላዩ የግብጽ መልከዓ ምድር ስፋት 6% የሚሆነውን ክፍል ይሸፍናል፡፡ ክልሉ ሦስት ማእዘን ቅርጽ ያለው ሲሆን መሰረቱ በስተሰሜን የሜድትራኒያን ባህር ዳርቻ ሲሆን ጠረፉ በስተደቡብ ራስ ሙሐመድና አቀባ ባህረሰላጤ በስተምስራቅ የስዊዝ ባህረ ሰላጤና በስተምዕራብ ደግሞ የስዊዝ ካናል ያዋስኑታል፡፡

የሲናይ ተራራዎች ወደሦስት ዋናዋና ክፍሎች ይከፈላሉ፡፡

ደቡባዊው ክፍል

የሲናይ ደቡባዊ ክፍል ግራኒታዊ እጅግ ረዣዥም ተራሮችን ያካተተ ሲሆን ጠጣርና ኮረኮንቻማ ክልል ነው፡ በዚሁ ክልል በግብጽ ምድር በጣም ረዥሙ የሚባለውና ከባህር ወለል በላይ 2637 ሜትር ከፍታ ያለው የሳንት ካትሪን ተራራ ይገኝበታል፡፡

መካከለኛው ክፍል

በዚህ ክልል-ቲህ- በመባል የሚታወቀው የማእከላዊ ሲናይ ተራራዎች ይገኛሉ፡፡ የነዚህ ተራራዎች ተፋሰሶች ደረጃ በደረጃ ወደ ሜድትራኒያን ባህር ዳርቻ ያቆለቁላሉ፡፤

ሰሜናዊው ክፍል

በዚህ ክልል ከቲህ ተራራና ከሜድትራኒያን ባህር ዳርቻ መካከል ያለውን ክፍል ያቀፈ ሲሆን ሜዳማ ክልሉ ከደቡባዊ ተራራዎችና ከማእከላዊ ክልሎች የሚመጡ የዝናብ ውሃዎችን በማከማቸት ይታወቃል፡፡

የሀገሪቱ ቋንቋ

የሀገሪቱ ብሄራዊ ቋንቋ አረብኛ ሲሆን በተለያየ የንግድ አካባቢዎች እንግሊዘኛና ፈረንሳይኛ ቋንቋዎችም አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡

የህዝብ ቁጥር

እ.ኤአ. በ2017 በተደረገ የህዝብ ቆጠራ የግብጽ ነዋሪዎች ቁጥር ወደ104.2 ሚሊዮን ከፍ ብሏል፡፡

የመገበያያ ገንዘብ

የግብጽ የመገበያያ ገንዘብ የግብጽ ፓውንድ ይባላል፡፡ የሀገሪቱ ማእከላዊ ባንክ የሚያትመው አንድ ፓውንድ  100 ቂርሽ -ሳንቲም- ያካትታል፡፡ የግብጽ የመገበያያ ገንዘብ የግብጽ ፓውንድ ለመጀመሪያ ጊዜ በሙከራ መልኩ እ.ኤ.አ. በ1834 የታተመ ሲሆን በይፋ አገልግሎት መስጠት የጀመረው በ1836 ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት (2018) የግብጽ ፓውንድ ዋጋ (1 ዶላር 17 ፓውንድ ከ60 ቂርሽ) ይደርሳል፡፡

የሀገሪቱ ብሄራዊ ባዕል

የግብጽ ብሄራዊ ባዕል በየዓመቱ ጁላይ 23 የሚከበር ሲሆን ጁላይ 23 1952 የተካሄደውን አብዮት ምክንያት በማድረግ ነው፡፡

የግብጽ ሰንደቅ ዓላማ                                                                                                  

የግብጽ ሰንደቅ ዓላማ ሦስት አኩል መጠን ያላቸው ቀለማትን ያካተተ ሲሆን የላይኛው መስመር ቀይ መካከለኛው መስመር ነጭና የታችኛው መስመር ደግሞ ጥቁር ቀለም አለው፡፡ በሰንደቅ ዓላማው ማእከላዊ ክፍል በወርቃማ ቀለም የንስር ስእል ተቀምጧል፡፡

 

የግብጽ ዋና ከተማ

የግብጽ ዋና ከተማ ካይሮ በነዋሪዎች ቁጥር ብዛት በዓረቡ አለምና በአፍሪካ የመጀመሪውን ደረጃ ይዛ ትግኛለች፡፡

ከተማዋ ከአለም አቀፍ መዲናዎች መካከል ጉልህ ቦታ ያላት የጥንት ከተማነች፡፡ ህችው ከአንድ ሺህ ዓመት በፊት የተቆረቆረችውታላቋ ካይሮ ከተማ  የሀገሪቱ መንግስት ማእካለዊ ከተማ ነች፡፡ በከተማዋ ካሉ ጉልህ ገጽታዎች ፒራሚዶች፣ ስፊንክስ፣ ካይሮታወር፣ ላሕ ዲን ግንብ፣ የአል አዝሀር መስጊድ፣የሱልጣን ሐሰን መስጊድ፣ የባቢሊዮን ሽግ፣ የግብጽ ዚየም፣ስላማዊዚየም፣ የኮፕቲክ ዚየምና ችም ናቸው፡፡

የሀገሪቱ ዋናዋና ከተሞች

ከሀገሪቱ ዋናዋና ከተሞች በግንባር ቀደምነት ገኙት፡ ካይሮ ጊዛ፣አሌክሳንድያ፣ ፖር ሰኢድ፣ ስዊዝ፣ ሎግር፣ አስዋን፣ሁርጋዳ፣ ሼርም ሸኽ፣ መጥሩሕና መርሳ ዓለም ናቸው፡፡

 

የግዛት አከፋፈል

ግብጽ አረብ ሪፐብሊክ 7 ክፈለ ግዛቶች ያሏት ሲሆን፣ የግብጽ አጠቃላይ ስታትስቲክና ምደባ ማእከላዊ ድርጅት በቅርቡ ደረገውጥናት እነዚህ ግዛቶች በአቃላይ 27  ሀገራት 225 ከተሞች፣ 91 አስከ 837 ወረዳዎች፣ 4727 መንደሮችና 27 አዲስየተቆረቆሩ  ከተሞችና 636 ቋሚ ያልሆኑ የነዋሪ ክምችቶች ይካተቱባቸዋል፡፡

የሀገሪቱ ታሪክ

ግብጽ በአለም አቀፍ ደረጃ የታሪክ ማህደር ከመጀመሩ በፊት በጣም የጥንት ስልጣኔዎች ከመነጩባቸው አገሮች በመጀመሪያ ትጠቀሳለች፡፡ ክልደተ ክርስቶስ በፊት 110 ሺህ ዓመት በፊት በግብጽ ምድር በጥንታዊው የድንጋይ ዘመን መጨረሻ በስልጣኔ የላቁ ሰዎች ይኖሩባት እንደነበረ በጥናት ተረጋግጧል፡፡ ከ5500 ዓመታት በፊት ግብጻዊያን የእርሻን ዘዴ ተፈላስፈው ጥራጥሬ ያመረቱና እንሰሳትንገርተው መተዳደሪያ ደንብ አስቀምጠው የተረጋጋ ኑሮ መምራት መጀመራቸውና መንደሮች መመስረታቸውን አሁንም ጥናቶች በመረጃ አረጋግጠዋል፡፡

የጥንታዊቷ ግብጽ ታሪክ ከልደተ ክርስቶስ በፊት 3150 ላይ አንደጀመረ ይነገራል፡፡ ይኧውም ንጉሥ ሚና ላይኛውንና ታችኛውን ግብጽ አዋህዶ የመጀመሪያውን የፈርኦን ስርወ መንግስት ባዋቀረበት ወቅት ነበር፡፡ ከዚያም የተረጋጋ አስተዳደር የመሩ የተላያዩ ንጉሦች በዚሁ ስርወ መንግስት ተካተዋል፡፡ የጥንቱ የግብጽ ፈርኦናዊ ስልጣኔ ለአላም የሰብኣዊ ቅርስ በርከታ ወጤቶችን አበርክቷል፡፡ በዚህች አለም ታሪክ የመጀመሪያው ማእከላዊ አስተዳደር የተዋቀረው በአባይ ተፋስ አካባቢ ነበር፡፡ በሳይንስ፣ በሒሳብ፣ በምህንድስና፣ በህክምናና በሥነ ፈለክ ዘርፎች የፈጠራ ሥራም የተጀመረው በዚሁ በግብጽ ምድር በአባይ ተፋሰስ ክልል ነበር፡፡ የመጀመሪያ የከርስ ምድር ማዕድንም ወጥቶ አገልግሎት መስጠት የጀመረው በዚሁ አካባቢ ነው፡፡የአጀንዳ-ቀን መቁጠሪያ- የተፈለሰፈውና የሥነ ጥበብ ሥራ የተጀመረው በፒራሚድ ገንቢዎች ፈርኦናዊያን አማካይነት በር፡፡ ይህ የፈጠራ ሥራ በመካከለኛውና በአዲሱ የግብጽ አስተዳደር ዘመንም የቀጠለ ሲሆን በአዲሱ የአስተዳደር ዘመን የፈጠራ ሥራ ጡዘት ደርሶ እንደነበር ይታወቃል፡፡

በግብጽ የግሪክና የሮማን አስተዳደር የግንባታ፣ የባህልና የስልጣኔ ተሃዲሶ የተከናወነ ሲሆን በእርሻና በኢንዱስትሪ ዘርፍም የላቀ ብልጽግና ታይቶ ነበር፡፡ በወቅቱ የግብጽ መናገሻ የነበረችው አሌክሳንድሪያ በምስራቃዊ ሜድትራኒያን ካሉ የንግድና የኢንዱስትሪ ማእከላት የመጀመሪያውን ደረጃ ይዛ ነበር፡፡ የክርስትና እምነት ወደ ግብጽ በገባበት ወቀት ደግሞ የፈርኦናዊ ገጽታ ያለውን የህንፃ ግንባታና የሥነ ጥበብ ስራ ተስፋፍቶ እንደበር በአምስተኛው ክፍለ ዘመን የተገነቡና እስካሁንም ደረስ ያሉት ቤተክርስቲያኖች ይመሰክራሉ፡፡

ሙስሊሞች ግብጽን  ከከፈቱ በኋላ ደግሞ ሀገሪቱ ከኡመዊያን አስተዳደር ጀመሮ አስከ ኦተማኒያን አስተዳደር መጨረሻ ድረስ የአስተዳደር ማእከል ሆና ቆይታለች፡፡ አዲሲቷ ግብጽ የተመሰረተቺው እ.ኤ.አ. በሀገሪቱ ስልጣን በጨበጡት በሙሀመድ ዓሊ ዘመን ነበር፡፡ በጁላይ 1952 በተካሄደው አብዮት የንጉሳዊው አስተዳደር ከተወገደ በኋላ የመጀመሪያው ሪፐብሊክ አስተዳደር 1953 ተመሰረተ፡፡

በሀምሳዎቹና በስድሳዎቹ በገማል አብደል ናስር ዘመን ሀገሪቱ በተላያዩ መስኮች ሰፊ ብሄራዊ ምጥቀትን አስመዝግባለች፡፡ በአህጉራዊና አለም አቀፍ ደረጃም የሀገሪቱ ሚና በከፍተኛ ደረጃ ወደፊት ተራምዷል፡፡ በ2014 ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ የሀገሪቱ መሪ ሆነው ከተመረጡ በኋላ ደግሞ ሁለገብ የልማት እንቀቅስቀሴ በሀገሪቱ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በኢንዱስትሪ፣ በእርሻና በግንባታ ዘርፎች የተጀመሩት ብሄራዊ የሜጋ ፕሮጀክቶች ከፍተኛ ትኩረትን ስበዋል፡፡